የጥቁሮች ፣ በመጓጓዣ ላይ የሚደረግባቸው መድልዎ ፣ እንዲያበቃ በፍርድ ቤት ከተወሰነ

ታሪክን የኋሊት

ህዳር 4 2018

በአላባማ፣ ጥቁሮች በአውቶቡስ የፊት ወንበር ለመቀመጥ የተጣለባቸው ገደብ ፣በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲነሳ የተደረገው፣ በ1948 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡
በሞንቲጎመሪዋ አላባማ ከተማ ጥቁሮች በአውቶብስ ሲሳፈሩ ከመሐከለኛ ወንበር በኋላ እንጂ ከፊት ባለው ወንበር እንዳይቀመጡ የተከለከሉ ነበሩ፡፡
ጥቁሮች፣ በአውቶብስ የፊት ወንበር እንዳይቀመጡ የሚከለከለውን፣ ዘረኛ ፖሊሲ በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲቋረጥ፣ መነሻ የሆነችው ፣ ሮዛ ፓርክስ ናት፡፡
ሮዛ ፓርክስ፣ ለጥቁሮች መብት በሚደረገው እንቅስቃሴ፣ ንቁ ተሳታፊ የሆነች የአለባማ ከተማ ነዋሪ ነበረች፡፡
ሮዛ ከቤቷ ወደ ስራዋ ለመሄድ በተሳፈረችበት አውቶቡስ የፊት ወንበር ተቀመጠች፡፡
የአውቶቡሱ ሾፌር፣ ለጥቁሮች በተከለከለ ወንበር የተቀመጠችውን ፓርክሰን ወደኋላ እንድትሄድ አዘዛት፡፡
አልተቀበለችውም፡፡

በቁጣ ሊያስገድዳት ሞከረ፡፡ እምቢ አለች፡፡
ሮዛ ፓርክስ አመፀች፡፡
ሾፌሩ ለፖሊስ ተናገረ፡፡
ፖሊሶች እንድትለቅ ቢያዟትም ፣ እምቢ ስላለች ጣቢያ ወስደው አሰሩዋት፡፡
14 ዶላር መቀጫ እንድትከፍል ተነገራት፡፡
የሮዛ ፓርክስን መታሰር፣ በዘር መድልዎ የሚንገላቱት ጥቁር አሜሪካውያን በዝምታ አላለፉትም፡፡
የጥቁር ሴቶች ማህበር፣ የሮዛ ፓርክስን መታሰር ተቃውሞ ጥቁር ሴቶች ለመብታቸው እንዲነሱ የፁሑፍ ቅስቀሳ በተነ፡፡
“ገንዘብ ከፍለን ለምንሳፈርበት አውቶብስ ወንበር መለየታችን እንቃወማለን” የሚል የሰላማዊ አመፅ አድማ ተጠራ፡፡
የጥቁሮች አብያተ ክርስቲያን ካህናትም፣ ድርጊቱን ለመቃወም ማርቲን ሉተር ኪንግ የሚመራው አስተባባሪ ኮሚቴ አዋቀሩ፡፡
በአላባማ ፣ ማንኛውም ጥቁር በአውቶቡስ እንዳይሳፈር ጥሪ ተደረገ፡፡


የሥራ ቦታቸው፣ ራቅ ያሉት፣ በጧት ተነስተው በእግር እንዲሄዱ ፣ መኪና ያላቸው ጥቁሮች ለሌሎቹ እገዛ እንዲያደርጉ ተወሰኖ ተግባራዊ ሆነ፡፡
ጥሪውን ሁሉም ጥቁሮች ተቀብለው፣ አውቶቡስ የሚሳፈር ጠፋ፡፡
ለወራት አድማው በመቀጠሉ፣ በመጓጓዣ ያለው ንግድ በኪሳራ አሽቆለቆለ፡፡
ባለሀብቶች፣አውቶብሶቻቸውን ለማቆም በመገደዳቸው፣ የመንግስት ግብር በእጅጉ ቀነሰ፡፡
ኪሳራውንና የአድማውን መጠንከር ያየው፣ የአላባማ ፍርድ ቤት፣ መድልዎው ፀረ ህገ መንግስት ስለሆነ እንዲቋረጥ ወሰነ፡፡
ግን አስፈፃሚው፣ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ ስላለ ፣ተግባራዊ ለማድረግ እግሩን ጎተተ፡፡
አድማው ተጠናከረ፡፡
በአውቶብስ ላይ ያለው የቀለም ልዩነት ገደብ እንዲነሳ የባለሀብቶቹ ጭምር ፍላጎት ሆነ፡፡
ይግባኙን የተመለከተው፣ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፣ ህዳር 4 ቀን 1949 በመጓጓዣዎች ላይ ጥቁሮችን የሚያስገልለው ህግ ፣ ፀረ መንግስት ስለሆነ፣ እንዲፋቅ የሥር ፍርድ ቤት የወሰነውን አፀና፡፡

ጥቁሮች በወንበር መቀመጫ ልዩነት እንዳይደረግባቸው በመላ አሜሪካ የሚከበር ውሳኔ ሆነ፡፡
የጥቁሮች በአውቶብስ ያለመሳፈር አድማ፣ አንድ አመት ያህል ቆይቷል፡፡
በውሳኔው መሰረት ፣ አውቶብሶች ስራ ሲጀምሩ ሮዛ ፓርክስ በፊተኛው ወንበር ተቀምጣ ተሳፈረች፡፡
ሮዛ ፓርክስ፣ ባደረገችው አሻፈረኝ ባይነት የአሜሪካ ምክር ቤት “የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ቀዳማዊ እምቤት” የሚል ማዕረግ ሰጥቷል፡፡
ሮዛ ፓርክስ በ94 አመቷ አረፈች፡፡
የጥቁሮች ፣ በመጓጓዣ ላይ የሚደረግባቸው መድልዎ ፣ እንዲያበቃ በፍርድ ቤት ከተወሰነ ዛሬ 69 ዓመት ሆነው፡፡
እሸቴ አሰፋ

SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station in Ethiopia. We are proud to be Ethiopian and we love our country more than anything!

Sheger Radio | Sheger 102.1FM © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!


















#Ethiopia #ShegerFM #ShegerRadio #YekidameChewata #MeazaBirru #Mekoya #EsheteAssefa #TizitaZeaRada #TeferiAlemu #AbebeBalcha #ShegerCafe #ShegerWerewoch #ShegerShelf #ShegerMezenagna #WendimuHailu #ShegerSport #YealemQunqua #EndalkEnaMahider #AderechArada #Woyaddissabeba #GirmaFisseha #ማንን_ምን_እንጠይቅልዎ #መቆያ #የቅዳሜጨዋታ #ሸገርሬድዮ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: t.ly/Sheger

Website: t.ly/ShegerFM

YouTube: t.ly/SHEGER

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger FM 102.1 Radio is The First Private FM Radio Station in Ethiopia

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz Receive SMS online on sms24.me

TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.

Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.

Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.

TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.

Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.

@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.

By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.

Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.

Look for new videos or channels and share them with your friends.

You can start using our bot from this video, subscribe now to የጥቁሮች ፣ በመጓጓዣ ላይ የሚደረግባቸው መድልዎ ፣ እንዲያበቃ በፍርድ ቤት ከተወሰነ

What is YouTube?

YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.