የኢትዮጵያ የዋጋ ውድነት ከሌላው ሀገር የተሻለ መሆኑን ለማሳየት በመንግስት የሚጠቀ?

የካቲት 10/2018

ዕለታዊ የኑሮ ፍጆታዎች የገበያ ውድነት በየጊዜው እየተባባሰ መምጣት አሁንም የሸማቹ ማህበረሰብ ፈተና እንደሆነ ቀጥሏል፡፡

መንግስት በበኩሉ “ከኬንያ አንፃር የኛ የመብራት ታሪፍ ቅናሽ ነው፣ከሌሎች ሃገራት ሲነፃፀር የኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ተመጣጣኝ ነው፤ ኢትዮጵያ አነስተኛ የቴሌኮም የአየር ሰዓት ከሚሸጡ ሀገራት መካከል አንዷ ነች“ የሚሉ የቁጥር ንፅፅር ምላሾችን ሲሰጥ ይሰማል፡፡

ለመሆኑ መንግስት የኢትዮጵያን ገበያ ከሌላ ሀገር ጋር በማነፃፀር የኢትዮጵያ የዋጋ ውድነት ከሌላው ሀገር የተሻለ መሆኑን ለማሳየት የሚያደረገውን የምጣኔ ሃብት ማብራሪያ ባለሙያዎች እንዴት ያዩታል?

የፖለቲካል ኢኮኖሚ ባለሙያው ሸዋፈራሁ ሽታሁን የአንድ ሃገር የኑሮ ውድነት ከሌላ ሀገር የሚሻለው በቁጥሮች ንፅፅር መበላለጥ አይደለም ይላሉ፡፡

ባለሙያው ቁጥር ከብዙ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ መለኪያዎች አንዱ እንጂ የኑሮ ውድነትን መቀነስ እና መጨመርን የሚያሳይ አሳማኝ ማስረጃ እንዳልሆነ ያስረዳሉ፡፡

ሸዋፈራሁ ሽታሁን የሌላን ሃገር የዋጋ ንረት ከኢትዮጵያ ገበያ ጋር ለማነፃፀር የየሃገራቱ የነፍስ ወከፍ ገቢ እና ጂዲፒ (GDP) ይወስነዋል ይላሉ፡፡

ባለሙያው “ከሌሎች ሀገራት አንፃር የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅምስ ምን ያህል ነው“ ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

ሌላው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ፋሲል ጣሰው የአንድን ሃገር የኑሮ ውድነት ከሌላ ሀገር የገበያ ውድነት ጋር በቁጥር ብቻ ማነፃፀር የየሀገራቱን የገንዘብ አቅምና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ዝርዝር መረጃዎች ያላገናዘበ፣ከኢኮኖሚ ሳይንሱ ጋር የሚጋጭ ነው ይላሉ፡፡

ባለሙያው የዕለት ተዕለት ፍጆታዎችን “ማን በሀገሩ ያመርታል፤ማንስ ከውጭ ያስገባል“ የሚለው ታሳቢ መደረግ እንዳለበት ያስረዳሉ፡፡

ለዚህም “ከህዳሴ ግድብ ሃይል የምታመርተው ኢትዮጵያ፣ከጎረቤት ሃገር መብራት ከምትገዛው ሱዳን ለምንና እንዴት ትነፃፀራለች“ የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፡፡

ከቁጥር ንፅፅር ይልቅ ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገራት በተሻለ የሀገር ውስጥ ምርቷን ለመጨመር ምን ሰርታለች፣ የስራ አጥነትን እንዴት ለመቆጣጠር አስባለች የሚሉና ሌሎች የዋጋ ውድነትን የሚያረግቡ መሰረታዊ ሃሳቦች ንግግር እንዲደረግባቸው ባለሙያዎቹ መክረዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..

ንጋት መኮንን

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7 Receive SMS online on sms24.me

TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.

Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.

Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.

TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.

Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.

@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.

By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.

Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.

Look for new videos or channels and share them with your friends.

You can start using our bot from this video, subscribe now to የኢትዮጵያ የዋጋ ውድነት ከሌላው ሀገር የተሻለ መሆኑን ለማሳየት በመንግስት የሚጠቀ?

What is YouTube?

YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.