ከከቲክቶክ፣ ከዩቲዩብና ከመሳሰሉ ከመሳሰሉ፤ የዲጂታል መገልገያዎች የሚሰበሰብ ግብ?
ታህሳስ 16/2018እንደ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ ከመሳሰሉ የዲጂታል መገልገያዎች ገቢ የሚያገኙ ሰዎች ግብር እንዲከፍሉ አሰራር እየተዘረጋ መሆኑ ተሰማ፡፡
በማህበራዊ ሚዲያዎች ገቢ የሚያገኙ ሰዎችም ሆነ ተቋማት በገቢዎች ቢሮ መመዝገብ ፣ የግብር መለያ ቁጥር ማውጣት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡
ባለፈው ዓመት ተሻሽሎ በፀደቀው የገቢ ግብር አዋጅ በዲጂታል መንገድ ይዘቶችን እየፈጠሩ የሚሰሩ ሰዎች ከሚያገኙት ገቢ ላይ ግብር መክፈል እንዳለባቸው ተደንግጓል፡፡
በኢትዮጵያ ለሚኖሩ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ክፍያዎችን የሚያመቻች ማንኛውም የኦንላይን መድረክ፣ ለእያንዳንዱ ይዘት ፈጣሪ የከፈለውን የገንዘብ መጠን ጠቅሶ ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢያቸውን በየዓመቱ ሪፖርት ማድረግ አለበት የሚለውም ሌላው በአዋጁ የተካተተ ሃሳብ ነው።
የዚህ አፈፃፀም የሚወሰነው ገቢ ሰብሳቢው መስሪያ ቤት በሚያወጣው መመሪያና አሰራር መሰረት እንደሆነም ያስቀምጣል፡፡
ይህንን ተከትሎም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከእነዚህ ይዘት ፈጣሪዎችም ይሁን በኦላይን ከሚደረግ ንግድ ገቢ ለመሰብሰብ አሰራሮችን እየዘረጋ መሆኑን ነግሮናል፡፡
በዘርፉ ካለው ሃብት አንፃር እስካሁን በዲጂታል መንገድ ከሚሰራ ስራ መንግስት የሚያገኘው ገቢ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፤ ስለዚህ በዲጂታል መንገድ ገቢ የምታገኙ ሁሉ ገቢያችሁን እያሳወቃችሁ የሚጠበቅባችሁን ግብር እንድትከፍሉ ተብሏል፡፡
ይህ የማይሆን ከሆነ በቢሮው በኩል እየተዘረጋ ባለው አሰራር መሰረት ወደ ማስገደድ እንደሚገባ የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ሰውነት አየለ ነግረውናል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ቢሮው አደራጀሁት ባለው የስራ ክፍል ምርቶችንም ይሁን አገልግሎቶችን በኦላይን በማስተዋወቅ የሚሸጡ፣ የሚለውጡትንም እቆጣጠራለሁ ብሏል፡፡
የኦላይን ገቢን ወደ ግብር ስርዓቱ ለማስገባት በቢሮው የተጀመረው ስራ በቅርቡ ወደ ሙሉ ትግበራ ይገባል የተባለ ሲሆን ስራውን ከኢትዮ ቴልኮም፣ ከንግድ ቢሮ፣ ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር የሚሰራ መሆኑንም ከቢሮው ሰምተናል፡፡
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://youtube.com/@shegerfm1021radio?si=MIGhci0wINMYwCmw
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1
WhatsApp : https://whatsapp.com/channel/0029VaAOnG9J3juypE0M4G1O
X : https://x.com/shegerfm?s=2 Receive SMS online on sms24.me
TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.
Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.
Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.
TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.
Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.
@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.
By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.
Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.
Look for new videos or channels and share them with your friends.
You can start using our bot from this video, subscribe now to ከከቲክቶክ፣ ከዩቲዩብና ከመሳሰሉ ከመሳሰሉ፤ የዲጂታል መገልገያዎች የሚሰበሰብ ግብ?
What is YouTube?
YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.