ታሪክን የኋሊት - በሜጄር ጄኔራል ሲያድ ባሬ የተመሩ ወታደሮች ሥልጣን የጨበጡት በ1962 ዓ

ታሪክን የኋሊት
ጥቅምት 11 2018

በሜጄር ጄኔራል ሲያድ ባሬ የተመሩ ወታደሮች ሥልጣን የጨበጡት በ1962 ዓ.ም በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ከመፈንቅለ መንግሥቱ ቀደም ብሎ፣ በአገሪቱ ታሪክ 2ኛው ፕሬዝዳንት በነበሩበት አብድረሺድ ዓሊ ሸርመርኬ ላይ ፖለቲካዊ ግድያ ተፈፀመባቸው፡፡
በሜጄር ጄኔራል ሲያድ ባሬ የተመራው ወታደራዊ ስብስብ ላዕላይ አብዮታዊ ምክር ቤት ያለውን አካል ሰየመ፡፡

ሲያድ ባሬ የአድራጊ ፈጣሪው ምክር ቤት የበላይና የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆኑ፡፡
ራሳቸውን “ጓድ” ያሰኙት ሲያድ ባሬ የምንከተለው ፖለቲካዊና የአስተዳደር ዘይቤ ሳይንሳዊ ሶሻሊዝም ነው አሉ፡፡

ኢንዱስትሪዎች ፣ ባንኮችና ታላላቅ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ተወርሰው ወደ መንግስት ይዞታነት ተዛወሩ፡፡

ሲያድ ባሬ፣ እንደቀደምቶቻቸው ከኢትዮጵያ የኦጋዴን ግዛት ፣ ከኬንያ ሰሜን ምሥራቅ ክፍሏንና ጂቡቲን እንዳለ ወደ ሶማሊያ ጠቅልሎና ‹‹የታላቋ ሶማሊያን›› እንመሰርታለን የሚለው ፍላጎት ደጋፊ ነበሩ፡፡


በኢትዮጵያ ከአፄ ኃይለ ስላሴ ሥርዓት መወገድ በኋላ፣ በአገሪቱ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ግርግርና የእርስ በርስ ጦርነት ሲያድ ባሬ ለክፉ ውጥናቸው ዳር መድረሻነት የምቹ ምቹ ሆኖ አገኙት፡፡

የታላቋ ሶማሊያ እቅዳቸውን ሥራ ላይ ለማዋል በኢትዮጵያ ላይ መጠነ ሰፊ ወረራ ጀመሩ፡፡

በምስራቅ 700 በደቡብ 300 ኪ.ሜ ዘልቀው ገቡ፡፡

ግን እንደ ኃሳባቸውም አልሆነም፡፡
እንዲያውም በተቃራኒው የሶማሊያ ሠራዊት በተከላካዩ የኢትዮጵያ ጦር ወደመጣበት ተመለሰ፡፡

የሲያድ ባሬ የ “ ታላቋ ሶማሊያ” ቅዠት መከነ፡፡
ብልሽትሽቱ በወጣው የተዛባ ምጣኔ ሐብታዊ ፖሊሲ የተነሳ የሶማሊያ ኢኮኖሚ ወደቀ፡፡

የሕዝቡ የኑሮ ደረጃ አሽቀለቆለ፡፡

የሲያድ ባሬ አስተዳደር ጨቋኝነትና የሰብዓዊ መብት ረገጣው ሕዝቡን አስመረረው፡፡

ይሄና ሌላው ሌላው ብሶትና ምሬት ከኦጋዴኑ ጦርነት አሳፋሪ ሽንፈት ጋር ተነባብሮ፤ በሲያድ ባሬ ላይ አመፅ ጠራባቸው፡፡

አመፁ ወደ የእርስ በርስ ጦርነት አመራ፡፡

ሲያድ ባሬ በሥልጣናቸው ለመፅናት ተንገታገቱ፡፡ አልሆነላቸውም

አገር ጥለው ሸሹ፡፡

በመጀመሪያ ኬንያ ገቡ ፤ ከዚያም ወደ ናይጄሪያ ተሻገሩ፡፡

በተሰደዱበት ናይጀሪያ ሌጐስ ከተማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

አስክሬናቸው ወደ ሶማሊያ ተመልሶ የቀብር ሥርዓታቸው በአገራቸው ተፈፀመ፡፡

አገሪቱ ከሁለት አሥር ዓመታት ላላነሰ ጊዜ ያለ ውጤታማ ማዕከላዊ መንግሥት በሥርዓተ አልበኝነት ስትናጥ ቆየች፡፡

በአሁኑ ወቅት ሶማሊያ መንግሥት ቢኖራትም በአልሸባብ ፅንፈኛ ቡድን ተፅዕኖ አሁንም ከጦርነት አዙሪቷ አልወጣችም፡፡


ግዛቶቿም ለየራሳቸው መንግስት ሲሀኑ ሶማሌላንድ የራሷን መንግስት መስርታለች፡፡

ሲያድ ባሬ ወታደሮች አስተባብረው ስልጣን ከያዙ 56 ዓመት ሆነ፡፡
እሸቴ አሰፋ

SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station in Ethiopia. We are proud to be Ethiopian and we love our country more than anything!

Sheger Radio | Sheger 102.1FM © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!


















#Ethiopia #ShegerFM #ShegerRadio #YekidameChewata #MeazaBirru #Mekoya #EsheteAssefa #TizitaZeaRada #TeferiAlemu #AbebeBalcha #ShegerCafe #ShegerWerewoch #ShegerShelf #ShegerMezenagna #WendimuHailu #ShegerSport #YealemQunqua #EndalkEnaMahider #AderechArada #Woyaddissabeba #GirmaFisseha #ማንን_ምን_እንጠይቅልዎ #መቆያ #የቅዳሜጨዋታ #ሸገርሬድዮ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: t.ly/Sheger

Website: t.ly/ShegerFM

YouTube: t.ly/SHEGER

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger FM 102.1 Radio is The First Private FM Radio Station in Ethiopia

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz Receive SMS online on sms24.me

TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.

Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.

Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.

TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.

Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.

@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.

By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.

Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.

Look for new videos or channels and share them with your friends.

You can start using our bot from this video, subscribe now to ታሪክን የኋሊት - በሜጄር ጄኔራል ሲያድ ባሬ የተመሩ ወታደሮች ሥልጣን የጨበጡት በ1962 ዓ

What is YouTube?

YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.