እርግጠኛ ነኝ የናንተም ሕይወት ከዚህ አይለይም!

ከቀናት በፊት በሶሻል ሚዲያ ገፃችን ላይ አንድ ጥያቄ ጠይቀን ነበር::
ከተፖሰተበት ሰዓት አንስቶ ሶሻል ሚዲያው በቤተሰቦቻችን መልሶች ተጥለቅልቆ ነበር ያመሸው::

"ያው አውቄ ነው 10 ሰዎች ብቻ ነበር ኮመንት ያደረጉት"

ለማንኛውም
(የተወሰኑ መልሶችን ከ AI ጋር በማገዝ ቪድዮ ላይ ታነባቸዋለህ)
እና ሌሎችም...

ሁላችሁም መልሱን እንደመለሳችሁት ይሁንላችሁ ብንባልስ ግን አስባቹታል?

"---- ያለው ልጅ ምን ነበር የሚውጠው? "

ለማንኛውም በአጭሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ኑሮ በጣም አማራሪ እንደሆነ ከብዙዎቹ ኮመንት እና ከኔ ሕይወት መረዳት ይቻላል::

ግን ሁሌ ግርም የሚለኝን ነገር ልንገራችሁ
♦️ በጣም ተቸግረው በረሃብ የሚሞቱ ሰዎች ያሉት እኛው ሀገር ውስጥ ነው::
♦️ እንዲህ ሰው በግፊ የሚበላውም እኛው ሀገር ነው::

♦️ በገንዘብ እጦት ምክንያት የሚበተኑ ትዳሮች ያሉት እኛው ሀገር ነው::
♦️እንዲህ አይነት ቅንጡ ሰርጎችም የሚደገሱት እኛው ሀገር ነው::
♦️ ይሄም የታክሲ ሰልፍ - ይሄ መኪናም ያለው እዚቹ እኛው ሀገር ነው::

ምን ጉድ ነን ግን እኛ ኢትዮጵያዊያን?

እኔ እንደውም አንዳንዴ ሳስበው የውጭ የርዳታ ድርጅቶች የቀሩት በዚህ ምክንያት ይሆን እላለው::

- አስበው ለሆነ ቦታ እርዳታ ይዘው የመጡ ግለሰቦች ቁርጥ በግፊ የሚበላበት ሰፈር በኩል ሲያልፉ
(Meme: አል ሪሳላ እዚህስ በፍፁም ሊኖሩ አይችሉም)

- አስበው እድሜ ልክህን በረሃብ እና በጠኔ ኖረህ የሞትክ ለት ሙክት ሙክቱ ሲታረድ
(አታ በአለጌ ህዝቢ)

ኢትዮጵያን በአእምሮ በሽታ ግለፃት ብባል በምንም አልገልፃትም ነበር.... (አእምሮው የታል ሲጀመር)

እኔ ምለው ሰው ተስፋ አይቆርጥም? ተስፋ ማንቆርጠው ነገርስ!

ኑሮ እኮ እሽት ነው ያደረገን? ተቆልተናል እኮ ተወቅጠናል!
ተፈጭተን እኮ ፈልተናል!
ግራ ግብት እኮ ነው ሚለው?
እንደ አወቃቀጣችን ቢሆን እኮ ዱቄት ነበር መሆን የነበረብን? እኛ እናቴ ዝንጥ! ማሻአላህ!
ዘንጠን እኮ ነው የምንወጣው?

ችግር ረፍት የነሳን ምስኪኖች ጭራሽ እሁድን የረፍት ቀን ብለን ልንዝናና እንወጣለን! ሳምንቱን ሙሉ ምን ሰርተን ነው እሁድ የምናርፈው ቆይ? ሆ!

እሺ እሁድን ተውት! ለበዓል በግ የምናርደው ነገርስ? አሁን እኛ ቤት በዓል ነው ተብሎ በግ ይታረዳል! በግ!

እኔ በጉን ሳየው እንዴት እንደምቀና..... ተከፍሎት እኮ ነው ሚሞተው... እኔ እኮ ለመኖር ብር የለኝም!


♦️ አንዳንድ የከተማችንን ነዋሪዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ለማውራት ሞክሬ ነበር

(ኢንተርቪው ይገባል::)
- እኔ ግርም የሚለኝ ደሞዜ 5000 ብር ነው:: ተከራይቼ ነው የምኖረው:: አስቤዛ አሟላለሁ:: በዚያ ላይ በየቀኑ የታክሲ 20 20 ብር አወጣለሁ:: ልጄን ትምህርት ቤት አስተምራለሁ:: ቆይ ከየት አባቴ አምጥቼ ነው ግን ይህን ሁሉ የምከፍለው? አሁን እኔ መንገድ ላይ ብቻዬን እያወራሁ አይደለም እንደ ማርሽ ባንድ እየዘመርኩ ብሄድ ማነው ሚፈርድብኝ?

- ባክህ ምን ብዬ ልንገርህ? ስራ እንደሚሰራ ሰው በጥዋት ነው ከቤት የምወጣው:: ከዚያ ቀኑን ሙሉ የ አውራ ጎዳና ስሞች እና ኤምባሲዎች ስም እያነበብኩ እዞርና ሲመሽ በዚያው ወደ ቤቴ ዝንጥ ብዬ እገባለሁ:: ደሞ ከሁሉም ይበልጥ የሚያስቀኝ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ቁርስ ምሳዬን በልቼ ከሰዓት በርጫዬን ቅሜ ማታ ፓኬጅ ሞልቼ ፊልሜን እያየሁ እተኛለሁ:: የደላው አልመስልም? ቂቂቂ ስራ እኮ የለኝም!

- ያው እኔ ቲክቶከር ነኝ!..... በቃ
(ማለት? ስራ ምናምን የለህም)
ስራ የለኝም!
(ማለት... ከቲክቶክ የምታገኘው የጌም ብርስ? ማስታወቂያ አስተዋውቀህ የምታገኘውስ ብር)
ብራዘር እኔ ሕዝቤን ፈታ ማድረግ ነው አላማዬ መላ ምናምን አገኛለሁ እኮ.... ግን ምን መሰለሽ? ለኔ አንበሳና ዩንቨርስ ጊፍት የሚሰጡኝ ሰዎች ስራ የለም ኑሮ ምናምን እያሉ ሲያማርሩ እኔ ስራ አለኝ ብል ካልኩሌት አርገሽዋል ግን.... የገባሽ አይመስለኝም.... ለምን ላይቭ ላይ ማች እያረግን አናወራበትም ግን?
***.

ዝም ብዬ ሁኔታችንን ሳስበው ግርም ይለኛል:: ኑሮው ክብድ ብሎ ብሎ
"ብዙ ሃዘን ያለበት ኮመዲያን ሆነናል::"
ዝም ብላችሁ ካያችሁት ሁሉም እኮ ቀልደኛ ሆኗል:: ለዛም መሰለኝ ከፖስቱ ኮመንቱ ይበልጥ የሚያዝናናን::

ከሁሉም የሚገርመኝ ከምንቸገረው ችግር በላይ ችግራችንን የምንለምድበት ፍጥነት እኮ ነው!

♦️ እኔ ሽንኩርት 150 ብር ገብቶ በዜብራ ምትሻገር ሴት እንዴት እንደምታስቀኝ?

♦️ አሁን እኔ..... የወር ገቢዬን ሁለት እጥፍ የሚሆን ብር ወጪ እያደረግኩ....ነገ እንገናኛለን የምለው ነገር ግርም ይለኛል:: ነገ እኮ የለም.... የምን ነገ ነው?

♦️ አሁን አንድ የሩቅ ዘመድ አለኝ.... ስራ የለው.... ስራ ያለው ዘመድ እንኳን የለውም.... ባለፈው ታሞ ልንጠይቀው ሄደን አምልጦኝ አላህ አፊያ ያድርግህ እለዋለሁ "አሚን!" አላለም? እኔ እኮ ግርም ነው ሚለኝ.... አሚን አለኝ!
አላህዬ ይቅር ይበለኝ እኔ ብሆን ኖሮ እንዲህ ነበር ምተናነቀው! ሆ አሚን!

♦️አሁን ለታ ልጄ ትምህርት ቤት የቤት ስራ ሰጥተዋት መጣች! እኔ ልጄን እንዲያስተምሩልኝ ብዬ ነበር ምልካት:: እነሱ ለካ የኔን ሕይወት መበተን ነው አላማቸው::

ምናለበት አሁን ዝም ብለው ወርሓዊ ክፍያውን እጥፍ ቢያደርጉት? እንዴ? ዝም ብሎ ሁሉም ነገር እጥፍ በሚሆንበት ሀገር ዝም ብለው ክፍያ ከነገ ጀምሮ 200 እጥፍ ጨመረ ቢሉ ማን ይቃወማል?

የቤት ስራ ብለው እንደዚህ አእምሮ የሚያናጋ ጥያቄ ይዛ መጣች እኔ ደግሞ ምንድነው ብዬ እንደ ደህና አባት ነይ የቤት ስራ ላሰራሽ አልኩና ጥያቄው ምንድነው አልኳት?
"ነገ ምን መሆን ትፈልጋለህ?" አላለችኝም
2 ሰከንድ አላሰብኩም ለመመለስ
"ነገ ምን መሆን ትፈልጋለህ?"
"ሬሳ!"
(የለቅሶ meme)

ቀልዱስ ቀልድ ነው?

መፍትሄ
♦️ ለማንኛውም እኔ መታዘብ እንጂ መልስ መስጠት ሥራዬም አይደለም መልስም የለኝም:: ግን እኔንጃ ተቀራርበን ማውራት ግን ሳይኖርብን አይቀርም::

የመደብ ልዩነታችን በጣም ከመስፋቱ የተነሳ ከእኛ ሌላ መደብ ያለ አይመስለንም!

ድሃው ሃብታም ያለ አይመስለውም
ሀብታሙም.... ሃብታም ያለ አይመስለውም 😊

ለማንኛውም የምር ራሳችንን ለመመዘን ቁጭ ብንል ደስ ይለኛል::
ሃብታሙም ቢያንስ በግሉ የአንድ ሰው ሕይወት ለመቀየር ቢሞክር.

የኔ ብጤውም ችግሩን ከመልመድ ወጥቶ ራሱን ለመቀየር ቢጥር እንዴት ደስ ይል ነበር::

ቢያንስ ባይሳካ እንኳን እየሞከሩ መሞትን የመሰለ ፀጋ የለንም::
ዋናው ጤና ቢሆንም ጤንነት ከስንፍና ጋር ሳይሆን ከጀግንነት ጋር ነው የሚያምረው::

የረበና ሰላም በናንተ ላይ ይሁን🙏 Receive SMS online on sms24.me

TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.

Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.

Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.

TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.

Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.

@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.

By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.

Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.

Look for new videos or channels and share them with your friends.

You can start using our bot from this video, subscribe now to እርግጠኛ ነኝ የናንተም ሕይወት ከዚህ አይለይም!

What is YouTube?

YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.