ዛሬ ሹመታቸው በፓርላማ በየፀደቀላቸው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ዳኞች ምልመላ ሂ?
ታህሳስ 28/2018ዛሬ ሹመታቸው በጸደቀላቸው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ዳኞች ምልመላ ሂደት የሃይማኖት፣ የብሄር እና የክልል ኮታንም ሆነ ውጤትንም መሰረት አላደረገም የሚል ትችት ከፓርላማመ አባል ቀረበበት፡፡
ትችቱ የቀረበው ዛሬ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት 34 የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት ባጸደቀበት ወቅት ነው፡፡
የምክር ቤት አባሉ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ተሿሚዎች ያለፉበት መንገድ ግልጽ መሆኑን አንስተው የሃይማኖት ስብጥሩ ግን አካታችነት ይጎድለዋል፡፡
“ኢትዮጵያን አይመስሉም፤ ይህም ኢትዮጵያን የሚመስሉ ተቋማት ግንባታ ሂደት ላይ እንቅፋት አይሆኑም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
የምክር ቤት አባሉ በማከልም ተሿሚዎች የሚበዙት ከአዲስ አበባ የተመለሱ መሆናቸውን አስታውሰው ከክልል የመጡት አምስት ብቻ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
ከሌላ አካባቢዎች ያልመጡት ልምድን ነው? እንዳንዶች የተሻለ ውጤት አምጥተውም ያላላፉ አሉ እሱ ከምን አንጻር ነው ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ሌላው የምክር ቤት አባል አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው የኡስታዝ ካሚል ሸምሱን ሃሳብ ተቃውመዋል፡፡
አለሙ (ዶ/ር) የተሿሚዎችን ዝርዝር ሰነድ መመልከታቸውን አስረድተው ዳኛ መመደብ ያለበት በብቃት ብቻ ነው ብለዋል፡፡
የዳኛነት ስራ በኮታ ሳይሆን በብቃት ነው መመዘን ያለበት ሲሉም አክለዋል፡፡
በምክር ቤቱ የፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኢሳ ቦሩ በበኩላቸው ዳኞቹ የተመለመሉት በብቃታቸው ፣ ፈተናውንም አልፈው፤ መስፈርቱንም አሟልው ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዳኞቹ በመጀመርያ ፍርድ ቤት በነበራቸው የስራ ዘመንም ጥሩ ስነ ምገባር ያላቸው በችሎታቸውም የተመሰገኑ ናቸው ብለዋል፡፡
ፍርድ ቤትም ኢትዮጵያን እንዲመስል እየተደረገ መሆኑን አቶ ኢሳ ተናግረዋል፡፡
ሌላው የምክር ቤት አባል አቶ ዘካሪያስ ኤርኮላ በዳኞች አስተዳዳር ጉባዔ በኩል ፍርድ ቤቶች ነጻ እና ገልልተኛ ሆነው እንዲሰሩ ከህግ ማሻሻያ ጀምሮ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አስረድተው ዛሬ የተሾሙት ዳኞች ብርካታ ፈተናዎችን አልፈው መመጥታታቸውን ጠቁመዋል፡፡
አቶ ዘካሪያስ ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ያላለፉት ለምድነው ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ ምናልባት የስነ ምግባር ጉድለት ኖሮባቸው ይሆናል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው የፈተና አሰጣጡ እና የልየታ ስራው ትክክለኛውን መንገድ የተከተለ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም ምክር ቤቱ የፌዴራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት ለማጽደቅ የቀረበውን ውሳኔ ሀሳብ በእንድ ደምጸ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምጻ አጽድቋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://youtube.com/@shegerfm1021radio?si=MIGhci0wINMYwCmw
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1
WhatsApp : https://whatsapp.com/channel/0029VaAOnG9J3juypE0M4G1O
X : https://x.com/shegerfm?s=2 Receive SMS online on sms24.me
TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.
Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.
Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.
TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.
Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.
@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.
By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.
Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.
Look for new videos or channels and share them with your friends.
You can start using our bot from this video, subscribe now to ዛሬ ሹመታቸው በፓርላማ በየፀደቀላቸው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ዳኞች ምልመላ ሂ?
What is YouTube?
YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.