ባይደን በጣሊያን የቡድን ሰባት አባል ሀገሮች መሪዎች ጉባዔ ናቸው

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ዛሬ ሐሙስ በጣሊያን አፑሊያ ከተማ ከቡድን ሰባት አባል ሀገሮች መሪዎች ጋር ጉባዔ ላይ ናቸው፡፡ በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ሀገሮች መሪዎቹ አውሮፓ እና መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ ጦርነቶች እየተካሄዱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ያለውን የዓለም ጸጥታ ጉዳይ ይወያያሉ፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና ፉክክርም የጉባዔው ትኩረት እነደሚሆን ተመልክቷል፡፡
መሪዎቹ ቅንጡው ጉባዔው የሚካሄድበት ቅንጡው ቦርጎ ኢኛትዚያ (Borgo Egnatzia) መዝናኛ ሲደርሱ የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ተቀብለዋቸዋል፡፡ አክራሪ ቀኝ ክንፉ የሜሎኒ ፓርቲ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተካሄደው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ 29 ከመቶ ድምጽ ያገኘ ሲሆን ጠንከር ያለ ድጋፍ አግኝተው የወጡ ብቸኛዋ የዋና የምዕራብ አውሮፓ ሀገር መሪ አድርጓቸዋል፡፡
ባይደን በሌላ በኩል በድጋሚ ለመመረጥ የሪፐብሊካን ፓርቲው ዕጩ እንደሚሆኑ ከሚጠበቁት ከቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ጋር ብርቱ ፉክክር ላይ ሲሆን በግልም አስቸጋሪ ጉዳይ ገጥሟቸዋል፡፡ በጣሊያኑ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ከመነሳታቸው በአንድ ቀን ቀደም ብሎ ማክሰኞ ዕለት ልጃቸው ሀንተር ባይደን የሱስ አስያዥ ቁስ ሱሰኛ ሆነው ሳለ መሣሪያ በመግዛት ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡
ያም ሆኖ ባይደን መሪዎቹን ለዩክሬይን 50 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት ለማግባባት ተስፋ በማድረግ ወደጉባዔው ተጉዘዋል፡፡ የቻይናን የኤሌክትሪክ መኪናዎች ጨምሮ በስትራተጂያዊ የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ አቅም ጉዳዮች ስምምነት እንደሚደርግ ተስፋ አድርገው ተጉዘዋል፡፡ የአውሮፓ ህብረት ባይደን ጣሊያን ከመግባታቸው በአንድ ቀን ቀደም ብሎ በቻይና የኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ ቀረጥ በመጣል እንደሚደግፋቸው ፍንጭ ሰጥቷል፡፡
ባይደን በተጨማሪም አፍሪካ ላይ መዋዕለ ነዋይ መመደብ፡ ዓለም አቀፍ ልማት እና የአየር ንብረት ጉዳዮችን ቁልፍ አጀንዳዎቹ ላደረገው የጂዮርጂያ መሎኒ አስተዳደር ፖሊሲ ድጋፋቸውን ገልጠዋል፡፡ በጉዳዮቹ ላይ በዛሬው የጉባዔው መክፈቻ ላይ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በማስከተል የጋዛ እና የዩክሬይን ጦርነቶች ላይም ተወያይተዋል፡፡
ቀን አክራሪዋ የጣሊያን ፖለቲከኛ መሎኒ አፍሪካዊያን ፍልሰተኞች በሜዲቴራኒያን ባሕር በኩል ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ ለመከላከል በባሕር ኅይል መርከቦች ይታጠር የሚል ጥሪ ማቅረባቸው ሲታወስ በአሁኑ ወቅት ደግሞ አፍሪካ ላይ ዓለም አቀፍ ኢንቬስትመንት በማጠናከር ያንን ግብ ለማሳካት ይፈልጋሉ፡፡ መሎኒ በርካታ የአእፍሪካ መሪዎችን በጉባዔው ላይ በታዛቢነት እንዲገኙ ጋብዘዋል፡፡ ከተጋበዙት መካከል የአልጄሪያ ፕሬዚደንት አብደልመጂድ ቴቡኒ፣ የቱኒዥያው ካይስ ሳኢድ፣ የኬኒያው ዊሊያም ሩቶ እና የሞሪታኒያው መሐመድ ኡልድ ጋዙዋኒ ይገኙባቸዋል፡፡


- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -
🔷 የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሊንኮችን በመጫን ይከተሉን።
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/voaamharic
ኢንስታግራም - https://www.instagram.com/voaamharic
X - https://www.twitter.com/VOAAmharic
ዌብሳይት - https://amharic.voanews.com
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ፡- https://www.youtube.com/voaamharic
የስልክ መሥመራችን 202-205-9942 የውስጥ መሥመር 14 ነው።
📜 ቪኦኤ-አማርኛ ስለ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ አፍሪካ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ዓለም አቀፍ በዲጂታል፣ በራዲዮና በቴሌቪዥን ዜናና ዘገባዎችን ለአድማጭና ለተመልካች ያቀርባል።
VOA Amharic reaches our audience on digital, radio, and TV, delivering news and content about Ethiopia, Eritrea, Africa, and the United States. We will also be bringing you Health Shows, Youth Shows, Democracy Field, Women’s Shows, and Sports Shows on different days, stay tuned. Receive SMS online on sms24.me

TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.

Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.

Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.

TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.

Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.

@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.

By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.

Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.

Look for new videos or channels and share them with your friends.

You can start using our bot from this video, subscribe now to ባይደን በጣሊያን የቡድን ሰባት አባል ሀገሮች መሪዎች ጉባዔ ናቸው

What is YouTube?

YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.