መንግስት በዚህ ዓመት ‘’ግብርናው ያድጋል’’ ብሎ የያዘው እቅድ በባለሞያዎች እንዴ?

ታህሳስ 24/2018

ግብርናው 64 ከመቶ የሰው ሀይል ያስተዳድራል፡፡

ዘርፉ 32 ከመቶ ለሀገራዊ ጠቅላላ ምርት አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡

ለሀገሪቱ የወጭ ንግድ 79 በመቶ የሚያበረክተው ግብርናው ነው፡፡

መንግስት የግብርናው ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት የ7.8 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግብ ትንበያ አስቀምጧል፡፡

በሌላ በኩል የግብርና ስራ በሚከወንባቸው አንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር አለ፡፡

በዚህም ምክንያት ገበሬው የግብርና ምርት ግብዓት ለማግኘት ሲቸገር ይስተዋላል፡፡

ታዲያ መንግስት በዚህ ዓመት ግብርናው ያድጋል ብሎ የያዘው እቅድ በባለሙያዎች እንዴት ይታያል? ያሉ ችግሮችስ እንዴት ይፈቱ?

በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የግብርና ኢኮኖሚ ምርምር ዳይሬክተር እና ተመራማሪ ታደለ ማሞ (ዶ/ር) ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ገበሬው ነፍጥ ካነሱ ሰዎች ጋር እርሻው እንዳይስተጓጎልበት ለማድረግ በማሰብ እንደሚነጋገር ያስረዳሉ፡፡

ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ገበሬዎቹ በዚህ መንገድ ከመግስት ሚላክላቸው የግብርና ግብዓት ያለምንም ችግር ለማግኘት ጥረት እንደሚያደርጉ ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ግብርናው ውስጥ እድገት አለ የሚባለው የሚታረሰው መሬት እያደገ እንጂ በአንድ ሄክታር የሚገኘው ምርት በሚፈለገው ደረጃ ሲያድግ አይታይምና ይህስ እንዴት ይታያል ስንል ባለሙያውን ጠይቀናቸዋል፡፡

ታደለ ማሞ (ዶ/ር) ዘርፉ የሚታረሰውም መሬት በማስፋትና በአንድ ሄክታር የሚገኘው ምርት በማሳደግ በሁለቱም መንገድ የሚገኘው ውጤት የዘርፉን እድገት ያሳያል ብለዋል፡፡

ባለፉት 10 ዓመታት በአንድ ሄክታር የሚገኘው የምርት መጠን እያደገ መምጣቱን ነግረውናል፡፡

ነገር ግን በምርም ተቋማትና በአርሶ አደሩ መካከል በአንድ ሄክታር የሚገኘው የምርት መጠን በእጥፍ ልዩነት አለው ይላሉ፡፡

እንደ ምሳሌነትም የበቆሎ ምርት በምርምር ተቋማት ውስጥ በሄክታር ከ80 ኩንታል በላይ የሚገኝ ሲሆን ገበሬው በአማካኝ እስከ 40 ኩንታል ነው የሚያገኘው ይህ ልዩነት ለማጥበብ በስፋት መሰራት አለበት ይላሉ፡፡

መንግስት በየዓመቱ የሚታረሰው መሬት ማስፋቱና በዓመት ከ2 ጊዜ በላይ የግብርና ስራ ለመከወን የሚሰራው ስራ ለዘርፉ እድገት ጥሩ ነው ነገር ግን በሄክታር የሚገኘው የምርት መጠንም ለማሳደግ ጠንክሮ መስራት አለበት ሲሉም መክረዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://youtube.com/@shegerfm1021radio?si=MIGhci0wINMYwCmw
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1
WhatsApp : https://whatsapp.com/channel/0029VaAOnG9J3juypE0M4G1O
X : https://x.com/shegerfm?s=2 Receive SMS online on sms24.me

TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.

Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.

Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.

TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.

Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.

@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.

By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.

Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.

Look for new videos or channels and share them with your friends.

You can start using our bot from this video, subscribe now to መንግስት በዚህ ዓመት ‘’ግብርናው ያድጋል’’ ብሎ የያዘው እቅድ በባለሞያዎች እንዴ?

What is YouTube?

YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.