የአማራ ክልልን ለቆ ወደ ስደት እና ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚፈልሰው ተወላጅ መጠን "?
ታህሳስ 17/2018ህጻናትን ጨምሮ የተሻለ ኑሮ ፍለጋ የአማራ ክልልን ለቆ ወደ ስደት እና ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚፈልሰው የክልል ተወላጅ መጠን "አጅግ አስደንጋጭ " መሆኑን የክልሉ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ።
በአማራ ክልል ባለፉት 5 ወራት ወደ ትምህርት ገበታቸው የተመለሱ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች 36 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ተናግሯል።
ይህ የተነገረው የትምህርት ቢሮው የክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ላይ የ5 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው።
የምክር ቤቱ አባላት ለተማሪዎች በትምህርት ገበታ አለመገኘት ጦርነቱን፣ ስደት፣ የቀን ስራ፣ በትምህርት ተስፋ መቁረጥን ጨምሮ የተለያዩ ምክንያቶችን ዘርዝረዋል፡፡
በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ወደ ትምህርት ያልተመለሱ ተማሪዎች አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንኳን መረጃ ማግኘት እንዳልተቻለ አስረድተዋል።
አንድ የምክር ቤት አባል የትምህርት መስኩ ችግር ውስጥ መሆኑን ጠቁመው በተለያዩ አካባቢዎች ከተማሪዎች ወላጆች እንኳን ልጆቹ የት እንዳሉ እንኳ መረጃ ማግኘት አንዳልተቻለ ተናግረዋል።
መረጃ ከሌለ ደግሞ እንዴት ነው እነዚህን ተማሪዎች መመለስ የሚቻለው? ሲሉ ጠይቀዋል።
በአማራ ክልል ከዚህ ቀደም የስደት ልማድ የሌለባቸው አካባቢዎች ሳይቀር አሁን ስደት ልምድ ሆኗል ተብሏል።
ይህም ልምምድ "በጣም አገደኛ ነው" ያሉት የምክር ቤት አባሉ ከክልሉ በስፋት "በአስራዎቹ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ናቸው ዓባይ በረሃን የሚሻገሩት እነዚህ ወጣቶች እየተሰደዱ ያሉት ደግሞ ስለ ቸገራቸው ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም" ብለዋል።
አምራች የሆነው የሰው ሃይል ነው ክልሉን ለቆ እየወጣ ነው፤ የሚሉት የምክር ቤት አባሉ ደጀን ከተማ ላይ "ለሁለት ሶስት ቀን ባደረግነው ምልከታ ባየነው ቁጥር በጣም ደንግጠናል "ሲሉ ተናግረዋል።
እነዚህ ልጆች ደግሞ በትምህርት በቅተው ስላልሆነ የሚሄዱት "የሰው ኬሻ ተሸካሚ እና እረኛ ነው የሚሆኑት" ብለዋል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ በአማራ ክልል ባለፉት 5 ወራት ወደ ትምህርት ገበታቸው የተመለሱ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች 36 በመቶ ብቻ ናቸው ብሏል።
ክልሉ በ5 ወራት ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ 7.4 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ባለው የሰላም እጦት ምክንያት መመዝገብ የተቻለው 4.3 ወይንም 58.2 በመቶ ብቻ መሆኑን የቢሮ ሃላፊ አቶ ጥላሁን በሪፖርታቸው አመላክተዋል።
በዚህም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ምዝገባ 85 በመቶ፣ በአንደኛ ደረጃ 58 በመቶ ፣ የሁለተኛ ደረጃ ደግሞ 36 በመቶ ብቻ መሆናቸውን አቶ ጥላሁን አስረድተዋል ።
ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱ ተማሪዎች ምጣኔ ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ቢሆንም በተለይ በጎጃም ዞኖች ችግሩ የከፋ እና የተመዝጋቢው መጠን 18 በመቶ ስለሆነ ልንወያይበት እና መፍትሔ ልንሰጠው ይገባል ብለዋል የትምህርት ቢሮው።
ይህም በክልሉ ብቁ የሰው ሃይል ማፍራት እና ተወዳዳሪነት ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል ተብሏል።
በአማራ ክልል በቀጠለው ወጊያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ስለ ወደሙ ተማሪዎች "በዳስ ስር ሆነው እንዲማሩ "ትዕዛዝ መስጠቱን ቢሮው ሃላፊ ተናግረዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ በበኩላቸው የክልሉ ትምህርት ችግር ውስጥ ያለ መሆኑን አስረድተዋል ከዚህን እንዴት መውጣት እንዲቻል በትብብር መስራት ያሻል ብለዋል።
ለተማሪዎች በትምህርት ገበታ አለመገኘት ዋነኛው ችግር ግን ግጭትን ማድረግ ተገቢ እንዳለሆነ የተናገሩት አቶ አረጋ ከግጭቱ በፊትም ትምህርት በክልሉ ችግር ውስጥ የነበረ ዘርፍ መሆኑን አመላክተዋል።
ርዕሰ መስተዳድር አረጋ በክልሉ አለ ስለተባለው ከፍተኛ ስደት እና ፍልሰት ግን በክልሉ መገናኛ ብዙሃን በተላለፈው ስብሰባ ላይ ሃሳብ አልሰጡም።
የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ መክፈቻ ንግግራቸው የክልሉ ኗሪ ጦርነት መሸከም እንደሰለቸው ጠቁመው ታጣቂዎች ወደ ሰላም እና ንግግር እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የቀጠለው ውጊያ በሁሉም ዘርፍ ላይ ቀውስ ማስከተሉን ያስተወሱት አፈ ጉባዔ ውጊያ የትም እንደማያደርስ ያለፉት 2 ዓመት ተኩል ጉዞ በቂ ማሳያ ነው ብለዋል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://youtube.com/@shegerfm1021radio?si=MIGhci0wINMYwCmw
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1
WhatsApp : https://whatsapp.com/channel/0029VaAOnG9J3juypE0M4G1O
X : https://x.com/shegerfm?s=2 Receive SMS online on sms24.me
TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.
Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.
Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.
TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.
Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.
@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.
By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.
Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.
Look for new videos or channels and share them with your friends.
You can start using our bot from this video, subscribe now to የአማራ ክልልን ለቆ ወደ ስደት እና ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚፈልሰው ተወላጅ መጠን "?
What is YouTube?
YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.