''ዩኒቨርሲቲዎች በለብለብ እያስተማሩ ማስመረቃቸውን እንዲያቆሙ''

ህዳር 2 2018

ዩኒቨርሲቲዎች በለብለብ እያስተማሩ ማስመረቃቸውን እንዲያቆሙ፣ ስኬታቸው የሚለካውም ባስመረቁት ተማሪ ብዛት ሳይሆን በተማሪዎቻቸው ብቃት ሊሆን እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) አሳሰቡ፡፡

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ በተደረገ ምልከታ ትምህርት ማስተማር ያልጀመሩ ዩኒቨርሲቲዎች አሉ ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲዎች የጥራት መለኪያ የሚሆነው በየዓመቱ በሚያስመርቁት የተማሪ ብዛት ሳይሆን በሚፈጥሩት ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት 34ኛው የትምህርት ጉባኤ በንግግር ሲከፍቱ ነው፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ እንዳሉት ኢትዮጵያም አሁን ቴክኖሎጂዎችን ከሌሎች ሀገራት እየቀዳች ነው ይህ ጥሩ ነው ነገር ግን ከወዲሁ ማሰብ ያለብን እስከመቼ ነው የምንቀዳው ሲሉ ጠይቀዋል ፡፡

የተማረ የሰው ሀይል ለማፍራትና ተወዳዳሪ ባለሞያ ለመፍጠር ከፈለግን ጥራት ያለው ትምህርት መስጠት አለብን ይህን ለማድረግ መሰረት እየጣልን ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርስቲዎች ከዚህ በኋላ ለተማሪዎቻቸው ዲግሪ ሲሰጡ ከሌላው አለም ጋር በዘርፋቸው ተመራቂዎችን ተወዳዳሪ ማድረግ ሲችሉ ብቻ ነው፤ ስራቸውን ተወጥተዋል ማለት የምንችለው ይላሉ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፡፡

የትምህርት ፍትሃዊነት ማለት በየቦታው ትምህርት ቤት መክፈት ሳይሆን የትምህርት ጥራት እንደ ሀገር እኩል ማዳረስ ስንችል ነው የከፈለው የተሻለ ትምህርት የሚያገኝና ድሃው ከዚያ ያነሰ የትምህርት ጥራት የሚያገኝ ከሆነ ነገ ላይ የተረጋጋ ሀገር እንዳንገነባ ሊያደርገን ይችላል ብለዋል፡፡

ያደጉ ሀገራት የተማረ የሰው ሀይል በተለየ መንገድ ወደ ሀገራቸው እየሳቡ ነው ያሉት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኢትዮጵያም የፈጠራ አቅም ላላቸው እና ብቁ ለሆኑ ተማሪዎች የሚሆን ስነ ምህዳር ከወዲሁ መፍጠር አለባት ይላሉ፡፡

በቅርብ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተዘዋውረን ስንመለከት የመጀመሪያ ሳምንት ክፍለ ጊዜን ያላስተማሩ መምህራን መኖራቸው ተገንዝበናል ዩንቨርስቲዎች ይህንን መቆጣጠርና ማስተካከል አለባቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በረከት አካሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇

🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
🐦X : https://x.com/shegerfm?s=2 Receive SMS online on sms24.me

TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.

Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.

Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.

TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.

Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.

@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.

By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.

Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.

Look for new videos or channels and share them with your friends.

You can start using our bot from this video, subscribe now to ''ዩኒቨርሲቲዎች በለብለብ እያስተማሩ ማስመረቃቸውን እንዲያቆሙ''

What is YouTube?

YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.