በኢትዮጵያ ከ35 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ከቀላል እስከ ከባድ የአዕምሮ ህመም እንዳለበት...

ታህሳስ 17/2018

በአማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ብቻ በዓመት 150,000 ሰው አዕምሮው እንደሚታከም ተነግሯል፡፡

በመላ ሀገሪቱም ከ35 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ከቀላል እስከ ከባድ የአዕምሮ ህመም እንዳለበት ባለሞያዎች ጥናት ጠቅሰው ይናገራሉ፡፡

ያለውን ችግር ያህል ግን ትኩረት እየተሰጠው አይደለም፡፡ ግንዛቤውም ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ የአዕምሮ ጤና ባለሞያዎች ማህበር ዋና ፕሬዝዳንትና በአማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የምርምር እና ስልጠና ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዘገየ ዮሐንስ የአዕምሮ ታማሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ነግረውናል፡፡

የአእምሮ ህመም መንስኤው ብዙ ቢሆንም የማህበራዊ ህይወት መመሰቃቀል፣ የኑሮ ውድነት፣ ጦርነት፣ ተፈጥሮአዊም ሆነ ሰው ሰራሽ ድንገተኛ አደጋዎችና ድባቴ ውስጥ የሚከሰቱ የአኗኗር ሁኔታዎች ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ባለሞያው አንስተዋል፡፡

ባለሞያው የአዕምሮ ህመም ሲባል ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ራሳቸውን የሳቱትን ብቻ የሚመስላቸው ሰዎች ብዙ ናቸው ያሉ ሲሆን ሰዎች ስራቸውን እየሰሩ፣ በትክክል እያሰቡና ከሰው ጋር እየተግባቡም ከአእምሮ ህመም ጋር ሊኖሩ ይችላሉ ብለዋል፡፡

ይህም ቀላሉ የአእምሮ ህመም ሲሆን ወደ ከፍተኛው ደረጃ ከመድረሱ በፊት ግን ሰዎች የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ኖሯቸው በጊዜ እንዲታከሙ አቶ ዘገየ መክረዋል፡፡

ምክንያቱ የማይታወቅ የተደጋገመ ድባቴ፣ ከሌላው ጊዜ በተለየ በቀላሉ ስሜታዊ መሆን፣ ከሰዎች ጋር መግባባት መቸገር፣ ስራን ተረጋግቶ መስራት አለመቻልና ሌሎችም መሰል ምልክቶች ለረጅም ጊዜ ከታዩ የህመሙ ማሳያዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ባለሙያው አስረድተዋል፡፡

መንግስትም ትኩረት ሰጥቶ በየጤና ጣቢያዎቹ የአእምሮ ጤና አገልግሎት እንዲያስፋፋ፣ ስለ የአእምሮ ጤና ለሰዎች በቂ ግንዛቤ እንዲሰጥና በዘርፉ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎችን በማፍራት ላይ እንዲሰራ አቶ ዘገየ ዮሐንስ መክረዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://youtu.be/c3Llj7YkRBo

ንጋት መኮንን

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://youtube.com/@shegerfm1021radio?si=MIGhci0wINMYwCmw
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1
WhatsApp : https://whatsapp.com/channel/0029VaAOnG9J3juypE0M4G1O
X : https://x.com/shegerfm?s=2 Receive SMS online on sms24.me

TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.

Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.

Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.

TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.

Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.

@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.

By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.

Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.

Look for new videos or channels and share them with your friends.

You can start using our bot from this video, subscribe now to በኢትዮጵያ ከ35 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ከቀላል እስከ ከባድ የአዕምሮ ህመም እንዳለበት...

What is YouTube?

YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.