በኬንያ በቀጠለው የተቃውሞ ሰልፍ ፖሊስ ናይሮቢ ውስጥ ሰልፈኞችን በአስለቃሽ ጭስ በተ?
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ከሥፍራው ባጠናቀረው ዘገባው እንዳመለከተው በቅርቡ የሃገሪቱ ፓርላማ ያረቀቀውን የቀረጥ ጭማሪ ረቂቅ ሕግ በመቃወም የተካሄዱትን እና የሰው ሕይወት የጠፋባቸውን ሰላማዊ ሰልፎች ተከትሎ፤ የኬንያ መንግስት የቀረበውን ረቂቅ ሕግ መሰረዙን ይፋ ቢያደርግም፤ በወጣቶች የሚመራ አዲስ የተቃውሞ ሰልፍ ግን ተጧጡፎ መቀጠሉ ታውቋል።ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ቀደም ሲል ‘በአገር ከሚፈጸም ክህደት የሚቆጠር’ የሚል ሥያሜ ሰጥተውት ለነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ምክኒያት የሆነውን አወዛጋቢ የፋይናንስ ረቂቅ ሕግ ፈርመው የማያጸድቁ መሆናቸውን ባለፈው ሳምንት ይፋ ቢያደርጉም፤ ሰልፈኞቹ ግን በአንጻሩ የተቃውሞ ዘመቻቸውን አጠናክረው መቀጠል መርጠዋል። በሌላ በኩል ለሁለት ሳምንታት በዘለቀው ሕዝባዊ ተቃውሞ 39 ሰዎች ሲገደሉ፣ ቁጥራቸው 361 የሚደርሱ ሰዎች የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው መሆኑን የኬንያ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በትላንትናው እለት አስታውቋል። ኮምሽኑ አያይዞም በተቃውሞ ሰልፍ አድራጊዎቹ ላይ የተወሰደውን የኃይል እርምጃም “ከመጠን ያለፈና እና ያልተመጣጠነ” ሲል አውግዟል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀደሙት የተቃውሞ ሰልፎች በተካሄዱባቸው የናይሮቢ ማዕከላዊ የንግድ መናሃሪያ አካባቢዎች የሚገኙ መደብሮች እና የንግድ ቤቶች ተዘግተው ሲውሉ፤ ፖሊስ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን በአካባቢው የተሰበሰቡ ሰልፈኞች ለመበተን አልፎ አልፎ አስለቃሽ ጭስ ሲተኮስ ታይቷል።
በተያያዘ የተቃዋሚዎች ጠንካራ ይዞታ በሆነችው የባህር ዳርቻይቱ ሞምባሳ፤ ኪሱሙ፣ ናኩሩ እና ኒሪ በተባሉ አካባቢዎች ቁጥራቸው በዛ ያሉ የተቃውሞ ሰልፈኞች እና የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴን የኬንያ ቴሌቭዥን አሳይቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሩቶ የኬንያ ወጣቶችን ቅሬታቸውን ለመስማት እና ለማነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ቢያመለክቱም፣ የሰልፉ አደራጆች ግን በተቃውሞ እንቅስቃሴው ‘እንቀጥላለን’ ሲሉ ዝተዋል።
በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈሯቸው ጽሁፎችም በያዝነው ሳምንት ተጨማሪ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ለማካሄድ ጥሪ አድርገዋል። “ሩቶ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ስልጣናቸውን እስኪለቅቁ ድረስ አናቆምም” የሚሉ አንዳንድ በራሪ ወረቀቶችም ታይተዋል።
- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -
🔷 የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሊንኮችን በመጫን ይከተሉን።
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/voaamharic
ኢንስታግራም - https://www.instagram.com/voaamharic
X - https://www.twitter.com/VOAAmharic
ዌብሳይት - https://amharic.voanews.com
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ፡- https://www.youtube.com/voaamharic
የስልክ መሥመራችን 202-205-9942 የውስጥ መሥመር 14 ነው።
📜 ቪኦኤ-አማርኛ ስለ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ አፍሪካ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ዓለም አቀፍ በዲጂታል፣ በራዲዮና በቴሌቪዥን ዜናና ዘገባዎችን ለአድማጭና ለተመልካች ያቀርባል።
VOA Amharic reaches our audience on digital, radio, and TV, delivering news and content about Ethiopia, Eritrea, Africa, and the United States. We will also be bringing you Health Shows, Youth Shows, Democracy Field, Women’s Shows, and Sports Shows on different days, stay tuned. Receive SMS online on sms24.me
TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.
Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.
Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.
TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.
Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.
@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.
By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.
Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.
Look for new videos or channels and share them with your friends.
You can start using our bot from this video, subscribe now to በኬንያ በቀጠለው የተቃውሞ ሰልፍ ፖሊስ ናይሮቢ ውስጥ ሰልፈኞችን በአስለቃሽ ጭስ በተ?
What is YouTube?
YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.