ሀብት ሳያሳውቁ የቀሩ የመንግስት ተሿሚዎችን ጉዳይ ለምርመራ ወደ ፍትህ አካላት መላኩ?
ታህሳስ 23/2018ማስመዝገብ ያለባቸውን ሃብት ሳያሳውቁ የቀሩ የመንግስት ተሿሚዎችን ጉዳይ ለምርመራ ወደ ፍትህ አካላት መላኩን የፌዴራል ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ተናገረ።
ሙስናን ለመከላከል መ/ቤቶች አሰራራችሁን ከእጅ ንክኪ ወደሆነ ኦን ላይን ይቀይሩ ተብሎ ስራ ሲጀመርም እንዲህ ባለውም መንገድ ብልሹ አሰራር መቀጠሉን ደርሼበታለሁ ብሏል ተቋሙ፡፡
የፌዴራል ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በየጊዜው የመንግስት ተሿሚዎችን፣ የህዝብ ተመራጮችን እና የሚመለከታቸውን የመንግስት ሰራተኞች ሃብት ይመዘግባል።
የተመዘገበውን ሃብት ትክክለኛነት የማጣራት ስራ እንደሚሰራም በኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ጥናት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ገዘኸኝ ጋሻው ተናግረዋል።
በዚህ የማጣራት ስራ ማስመዝገብ ያለባቸውን ሃብት ሳያስመዘገቡ የቀሩ የመንግስት ተሿሚዎች እንዳሉ አረጋግጠናል ብለዋል።
የእነዚህ ተሿሚዎች ጉዳይ ለምርመራ ወደ ፍህት አካላት መላኩን ጠቅሰዋል።
የሃብት ምዝገባው ሙስናን አስቅድሞ የመከላከል ስራ አንዱ አካል ነው የሚሉት አቶ ገዘኸኝ ሌሎች የቅድመ ሙስና መከላከል ተግባራትም እንዳሉ ተናግረዋል።
የቅድመ ሙስና መከላከል ጥናቶችን ማካሄድን እንደ አብነት ጠቅሰዋል።
በዚህ ስራ ደግሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ 49 ነጥብ 8 ሚሊየን ካሬ ሜትር መሬት ከምዝበራ ማዳን ችለናል ብለዋል።
ምዝበራን ለመከላከል ከሚቀርቡ ምክረ ሃሳቦች አንዱ አሰራሮችን በቴክኖሎጂ የታገዙ እንዲሆኑ ማድረግ የሚል ነው።
አቶ ገዘኸኝ በበኩላቸው የሰዎች አመለካከትም አብሮ ካልተቀየረ አሰራሮች በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ በማድረግ ብቻ ለውጥ ማምጣት ሊያስቸግር ይችላል ብለዋል።
እንደማሳያም በአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት በኤሌክትሮኒክ የግዥ ስርአት ላይ ያጋጠመውን ክስተት ጠቅሰዋል።
ኮሚሽኑ የመንግስት ተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጠጥ ሁኔታ ለማወቅም ጥናቶች እንደያካሂድ ሰምተናል።
በዚህ ጥናት 408 የመንግስት ተቋማት ላይ ችግር እንዳለ ተረድተናል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በሙስና በጎርጎርሳውያኑ 2024 ከ137 ሀገራት 99ኛ ደረጃን ይዛ እንደምትገኝ የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽ መረጃን ጠቅሶ የፌዴራል ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ተናግሯል።
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://youtube.com/@shegerfm1021radio?si=MIGhci0wINMYwCmw
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1
WhatsApp : https://whatsapp.com/channel/0029VaAOnG9J3juypE0M4G1O
X : https://x.com/shegerfm?s=2 Receive SMS online on sms24.me
TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.
Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.
Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.
TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.
Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.
@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.
By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.
Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.
Look for new videos or channels and share them with your friends.
You can start using our bot from this video, subscribe now to ሀብት ሳያሳውቁ የቀሩ የመንግስት ተሿሚዎችን ጉዳይ ለምርመራ ወደ ፍትህ አካላት መላኩ?
What is YouTube?
YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.