ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ የሄሞራጂክ ፊቨር በሽታ የተያዙ ሰዎች

ህዳር 8 2018

ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ የሄሞራጂክ ፊቨር በሽታ ተከስቶ በበሽታው የተያዙ ሰዎች መኖራቸውን የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባወጡት መረጃ ተናግረዋል፡፡

በጂንካ የተከሰተው በሽታ መንስኤው ማርበርግ ቫይረስ መሆኑ ተነግሯል።

ስለ ህመሙ ምንነትና መደረግ ያሉባቸውን ጥንቃቄዎች በተመለከተ ባለሙያ አነጋግረናል ዶክተር አሸብር መዘነ በወላይታ ሶዶ የእንያት ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር እና ጠቅላላ ሐኪም ናቸው፡፡

ሄሞራጂክ ፊቨር በሽታ ወረርሽኞችን ከሚያስከትሉና አደገኛ ከሚባሉ ህመሞች ውስጥ አንዱ በመሆኑ በጊዜ ለመቆጣጠርና ስርጭቱንም ለመቀነስ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሄሞራጂክ ፊቨር በተለያዩ አይነት ቫይረሶች የሚመጣ መሆኑን የሚናገሩት ዶ/ር አሸብር አሁን ላይ በተደረገው ምርመራ የሚያስከትለው ቫይረስ መለየት ተችሏል፤ የቫይረሱ መነሻ በተለይ ከሌሊት ወፎች እና ከዱር እንስሳቶች ጋር በሚኖር ንክኪ የሚመጣ ነውም ይላሉ፡፡

በበሽታው የተያዙ ሰዎች የተለያዩ ምልክቶች እንደሚያሳዩ የሚናገሩት ዶ/ር አሸብር ምልክቶቹ የሚታዩበት ጊዜ አንዳንዴ ረዘም ብለው የሚቆዩ በመሆኑ ጥርጣሬ ያለው ሰው ለሌሎች ሰዎች እንዳያስተላልፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

በአብዛኛው ምልክቶችን የሚታዩት ወዲያው ላይሆን ይችላል፤ አንዳንዶች እስከ 21 ቀን ድረስ ምንም ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ የተወሰኑት ደግሞ በሁለተኛው ሳምንት አካባቢ ዋነኛ ሚባሉትን ምልክቶች ያሳያሉም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሽታው በተለያዩ መንገዶች እንደሚተላለፍና በበሽታው ከተያዙ ሰዎች የሚወጡ ፈሳሾች ማንኛውም አይነት ፈሳሽ ተከትሎ የሚኖር ንክኪ በተለይም ፈሳሹ ወደ ሰውነት በተለያዩ መንገዶች ከገባ አይን፣ አፍንጫ እና አፍ አካባቢ ከተነካካ የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

አልፎ አልፎም ሁሉም ምልክቶች በአንድ ላይ ተከስተው ታማሚውን እስከ ራስ መሳት ደረጃ ሊያደርሱት ይችላሉ የሚሉት ባለሙያው በዋናነት ቫይረሱ የደም ቧንቧ ላይ ጉዳት በማድረስ እስከሞት አደጋ ሊያስከትል ይችላል ይላሉ፡፡

በተለይ ህክምና አካባቢዎች ላይ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች በተለያየ መንገድ የመጋጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ስለሆነ አገልግሎትን በሚሰጡበት ጊዜ ሊከላከሉ የሚችሉባቸውን የፊት መሸፈኛ ጓንት ጨምሮ ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል የሚያስችሉ አለባበሶችን መከተል አለባቸው ተብሏል፡፡

የበሽታው ምልክት የታየበት ወይም በበሽታው ከተጠረጠሩ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋማት በመሄድና በወቅቱ ምርመራ በማድረግ ከከፋ ጉዳት እንዲጠበቁ የጤና ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡

ለጊዜው የማርበርግ ቫይረስን የሚያጠፋ የተረጋገጠ መድኃኒት ወይም ክትባት ባለመኖሩም ጥንቃቄው ላይ መበርታት ይገባል ተብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ..

ምህረት ስዩም

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇

🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
🐦X : https://x.com/shegerfm?s=2 Receive SMS online on sms24.me

TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.

Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.

Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.

TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.

Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.

@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.

By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.

Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.

Look for new videos or channels and share them with your friends.

You can start using our bot from this video, subscribe now to ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ የሄሞራጂክ ፊቨር በሽታ የተያዙ ሰዎች

What is YouTube?

YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.