የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ወይዘሮ ኢንድራ ጋንዲ በጥይት ተደብድበው የተገደ?
#ታሪክንየኋሊት #Indira_Gandhi #EsheteAssefaታሪክን የኋሊት
ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ/ም
የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ወይዘሮ ኢንድራ ጋንዲ በጥይት ተደብድበው የተገደሉት ፣ የዛሬ 41 ዓመት በዛሬው ቀን ነበር፡፡
ኢንድራ ጋንዲ የተገደሉት ፣ የሲክ ዝርያ ባላቸው ሁለት ጠባቂዎቻቸው ነበር፡፡
ኢንድራ ጋንዲ ፣ አባታቸው ፣ የተለያዩ ጎሣ ሃይማኖት ያላቸውን ሕዝቦች አንድ አድርገው ሕንድን ለማጠናከር የታገሉት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃዋሃራል ኔህሩ ናቸው፡፡
ኢንድራ ጋንዲ ፣ ከልጅነታቸው ጀምሮ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር አባታቸውን የአስተዳደር ስልት እየተመለከቱ አደጉ፡፡
በ49 አመት እድሜያቸው፣ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆኑ፣ በአባታቸው ጊዜ የነበሩት የመከፋፋል የጎሣ ልዩነት ችግሮች ተጋረጡባቸው፡፡
በሥልጣን ዘመናቸው የሕንድን የምጣኔ ሐብት በማሳደግና ከፓኪስታን ጋር የተደረገውን ጦርነት በአሸናፊነት ለመወጣት ችለዋል፡፡
በሥልጣን ቆይታቸው አላሰራ አሉኝ ያሏቸውን ተቃዋሚዎችና የሲቪል መብት ተከራካሪዎች፣ ዘብጥያ በማውረዳቸው ተቃውሞ በረከተባቸው፡፡
ስልጣን ከያዙ አስራ አንድ አመት በኋላ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተደረጉ፡፡
ኢንድራ ጋንዲ፣ በፖለቲከኞች የተነቀፉ ቢሆንም፣ አብዛኛው ሕዝባቸው ግን በፈፀሟቸው የማህበራዊ እድገት እቅዳቸው፣ ይደግፋቸው ነበር፡፡
ስለዚህ ከስልጣን ከወረዱ ሶስት አመት በኋላ በሰፊ የህዝብ የድጋፍ ድምፅ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸው ተመለሱ፡፡
ለመገደላቸው እንደምክንያት የሚጠቀሰው፣ የሲክ ጎሳዎች የተከበረና የተቀደሰ ብለው በሚያምኑት ፣ቤተ መቅደስ፣ ወታደር ገብቶ የሀይል ርምጃ እንዲወሰድ በማዘዛቸው ነው፡፡
በፑንጃብ ግዛት የሚገኙት የሲክ ጎሣ አባላት፣ የራስ ገዝ አስተዳደር እንዲሰጣቸው ንቅናቄ ጀመረው ነበር፡፡
ጥያቄያቸው በሕንድ መንግስት ተቀባይነት አላገኘም፡፡
ንቅናቄውን ወደ ትጥቅ ትግል ያሸጋገሩት በቢሂንድራን ዋሌ የሚመሩት፣ ታጣቂዎች የተቀደሰ የተባለውን ወርቃማ ቤተ መቅደስ ተቆጣጥረው ምሽጋቸው አደረጉት፡፡
ድርድር ለማድረግ ቢሞከርም ስላልተሳካ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢንድራ ጋንዲ የመከላከያ ወታደሮች በሀይል እንዲቆጣጠሩት አዘዙ፡፡
ወታደሮች፣ ወርቃማውን ቤተ መቅደስና በአካባቢው ያሉ ሌሎች የሲክ ቤተ መቅደሶች በሀይል ተቆጣጠሩ፡፡
በተኩስ ልውውጡም ፣ የታጣቂዎቹ መሪና ታጣቂዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ሲቪሎችም ተገደሉ፡፡
“ቤተ መቅደሳችን ተደፈረ” የሚሉት ሲኮች ክፉኛ ተከፉ፡፡
ከተከፉት ሲኮችም አንደኛው የግል ጠባቂያቸው የሆነው ቢንት ሲንግ ነበር፡፡
ቢንት ሲንግ ለአንድራ ንጋዲ ታማኝ ጠባቂ ሆኖ ለረጅም ጊዜ አገልግሏል፡፡
ከቤተ መቅደሱ ዘመቻ በኋላ ፣ ሲንግ ከጠባቂነቱ ተነስቶ ወደ ሌላ ሥራ እንዲዛወር ተወስኖ ነበር፡፡
ኢንድራ ጋንዲ ግን ፣ ለብዙ ጊዜ ሲጠብቃቸው የነበረውን ሲንግ ፣ መጠርጠር ስላልፈለጉ አይሆንም አሉ፡፡
የሲክ ጎሳ አባል የሆነው ሲንግ ግን ከሌላው የሲንክ ጎሳ አባል የቤተ መንግስት ጠባቂ ጋር ሊያቅዳቸው አሴረ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩዋ ጥቅምት 21/1977 ረፋድ ላይ ከቤታቸው ወደ ስራ ለመሄድ፣ ግቢያቸውን እየወጡ እያሉ፣ ከፊታቸው ቆሞ በሽጉጥ በሶስት ጥይት መታቸው፡፡
ተባባሪው ስቱዋንትም 30 ጥይት አፈሰሰባቸው፡፡
በ33 ጥይት የተመቱት ኢንድራ ጋንዲ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም አልተረፉም፡፡
ያኑለት ሞቱ፣ ገዳዮቻቸው ተይዘው ቤንት እዚያው ሲገደል ሰቱዋት በፍርድ ተገደለ፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ኢንድራ ጋንዲ መገደል የተናደዱት ፣ደጋፊዎቻቸው የሲክ ጎሳዎችን አሳደዱዋቸው፡፡
3 ሺህ የሚሆኑትም ተገደሉ፡፡
ልጃቸው ራጂቭ ጋንዲ ስልጣናቸውን የተኳቸው ኢንድራ ጋንዲ ፣ ከተገደሉ ዛሬ 41 አመት ሞላው ፡፡
እሸቴ አሰፋ
SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station in Ethiopia. We are proud to be Ethiopian and we love our country more than anything!
Sheger Radio | Sheger 102.1FM © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.
ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡
ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
#Ethiopia #ShegerFM #ShegerRadio #YekidameChewata #MeazaBirru #Mekoya #EsheteAssefa #TizitaZeaRada #TeferiAlemu #AbebeBalcha #ShegerCafe #ShegerWerewoch #ShegerShelf #ShegerMezenagna #WendimuHailu #ShegerSport #YealemQunqua #EndalkEnaMahider #AderechArada #Woyaddissabeba #GirmaFisseha #ማንን_ምን_እንጠይቅልዎ #መቆያ #የቅዳሜጨዋታ #ሸገርሬድዮ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: t.ly/Sheger
Website: t.ly/ShegerFM
YouTube: t.ly/SHEGER
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Sheger FM 102.1 Radio is The First Private FM Radio Station in Ethiopia
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz Receive SMS online on sms24.me
TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.
Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.
Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.
TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.
Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.
@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.
By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.
Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.
Look for new videos or channels and share them with your friends.
You can start using our bot from this video, subscribe now to የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ወይዘሮ ኢንድራ ጋንዲ በጥይት ተደብድበው የተገደ?
What is YouTube?
YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.
 
                                     
                                     
                                     
                                     
                                     
                                     
                                     
                                     
                                    