በኢትዮጵያ የልባሽ ጨርቆች(ቦንዳ) ገበያ እና የሀገር ውስጥ አምራቾች!
ጥር 7/2018ገበያ ውስጥ ከሚገኘው አልባሳት ውስጥ 53 ከመቶ የሚሆነው ልባሽ ጨርቆች ወይም ቦንዳ ልብሶች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት አምራቾች ማህበር ያሰራው ጥናት ያሳያል፡፡
ጥናቱ የተደረገው ከ3 ዓመት በፊት በ2023 እንደጎርጎሮሲያኑ የዘመን አቆጣጠር ሲሆን የሚገቡት ልባሽ ጨርቆች በሶስት እንደሚከፈሉም ጥናቱ አሳይቷል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ከዓመት ዓመት የቦንዳ ልብሶች ገበያ ውስጥ እየጨመረ መምጣቱን የሚያሳይ ሲሆን የሀገር ውስጥ አምራቾችን እያዳከማቸው ይገኛል ተብሏል፡፡
በህገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጦ በሚገባው ልባሽ ጨርቅ ምክንያት መንግስት 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በአመት እንደሚያጣም ጥናቱ አሳይቷል፡፡
በጋርመንት ስራ ላይ የተሰማሩት አቶ ኤልያስ ሙሉጌታ የልባሽ ጨርቁ ጉዳይ ችላ በመባሉ አምራች ተቋማት እየተጎዳን ነው ብለዋል፡፡
በህጋዊ መንገድ ፋብሪካ ከፍተው ሰራተኛ ቀጥረው የሀገር ውስጥ ምርትን ለገበያ እያቀረቡ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ኤልያስ ልባሽ ጨርቁ ገበያውን እየተቆጣጠረው በመሆኑ ገገያው ውስጥ እየተፈተኑ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በህጋዊ መንገድ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ንግድ ፍቃድ አውጥተው ቦንዳ ልብሶችን የሚሸጡ ነጋዴዎች እንዳሉ የሚናገሩት አቶ ኤልያስ ከ3 አመት በፊት በተጠናው ጥናትም ይህ መረጋገጡን ጠቅሰዋል፡፡
በጥናቱ እንደተመለከትነው መርካቶ ጨምሮ ጨምሮ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የቦንዳ ልብስ ወይም ልባሽ ጨርቅ በስፋት እንደሚከፋፈል ተጠቅሷል፡፡
መርካቶ አጠና ተራ፣ ቦሌ እና 22 አካባቢ ከተጠቀሱ ስፍራዎች መካከል ናቸው፡፡
የተደረገው ጥናት ለመንግስት በወቅቱ ገቢ መደረጉን ከኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት አምራቾች ማህበር ያረጋገጠው ምላሽ እስካሁን አለመሰጠቱን ሰምቷል፡፡
አቶ ኤልያስ ሙሉጌታ በበኩላቸው የጨርቃ ጨርቅ ዘርፉ ኢትዮጵያ ውስጥ ገና እያደገ ነው ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል የልባሽ ጨርቁ ጉዳይ መንግስት አንድ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ሲሉም ጠየቀዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን በየጊዜው በቁጥጥር ስር የዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች ዝርዝር ሲያወጣ በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ልባሽ ጨርቆች መሆኑን በተለያዩ ጊዜ ከወጡ መረጃዎች ተመልክተናል፡፡
ጥናቱ መንግስት በኮንትሮባንድ የሚገባው ልባሽ ጨርቆችን በመቆጣጠር የሀገር ውስጥ የጨርቃጨርቅ ምርቶች እንዲጠነክሩ ማድረግ ላይ እንዲበረታ ጠይቋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..
YouTube : https://url-shortener.me/2DTR
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://url-shortener.me/2DTY
WhatsApp :https://url-shortener.me/2DU0
X : https://x.com/shegerfm?s=2
Website፡ https://www.shegerfm.com/
LinkedIn :https://url-shortener.me/2DU8
Tiktok : https://url-shortener.me/2DUB
Instagram : https://url-shortener.me/2DUD Receive SMS online on sms24.me
TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.
Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.
Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.
TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.
Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.
@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.
By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.
Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.
Look for new videos or channels and share them with your friends.
You can start using our bot from this video, subscribe now to በኢትዮጵያ የልባሽ ጨርቆች(ቦንዳ) ገበያ እና የሀገር ውስጥ አምራቾች!
What is YouTube?
YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.