በሩሲያ የኮሚዩኒስት ፓርቲው ቦልሼቪክ ስልጣኑን በሀይል ከወሰደ፣ ዛሬ 107 ዓመት ሞላው!
#ታሪክንየኋሊት #ShegerFMጥቅምት 27 2018
የሩሲያ ንጉሣዊ መንግስት የተካውን ጊዜያዊ መንግስት አስወግዶ፣ የቦልሼቪክ ፓርቲ ሥልጣን የተቆጣጠረው ፣ የዛሬ 108 ዓመት በዛሬው ቀን ነበር፡፡
በቦልሼቪክ ፓርቲ ስልጣን መያዝ ፣ለ300 አመታት ሩሲያን ሲመራ የቆየው የሮማኖቭ ስረወ መንግስት ማብቂያው ሆነ፡፡
ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን ያደረጀው የቦልሼቪክ ፓርቲ በሶሻሊስታዊ መርህ የሚመራና መሬት ላራሹ ፣ ዳቦ ለተራበው የሚሉ መሪ ቃሎችን በመያዝ የህዝቡን ስሜት ለመሳብ የቻለ ፓርቲ ነበር፡፡
በጊዜው የነበሩት፣ ንጉስ ዳግማዊ ኒኮላስ ከቀድምቶቹ የሩሲያ መሪዎች ጋር ሲነፃፀሩ ለቦታው የማይመጥኑ፣ የህዝቡን ፍላጎት ለማሟላት የሚተጉ አይደሉም፤ እየተባሉ ይተቹ ነበር፡፡
ዳግማዊ ኒኮላስ ፣ በ1888 ዓ.ም በሩሲያ የተቀጣጠለውን የህዝብ አመፅ ለማብረድ፣ የቻሉት የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ቃል ገብተው ነበር፡፡
ህገ መንግስቱን ለማሻሻል፣ በህዝብ የተመረጠ ምክር ቤት ለማቋቋም፣ ቃል ገብተው የተነሳውን አመፅ ለማቀዝቀዝ ቢችሉም፣ ተግባራዊ ሳያደረጉት ቀሩ፡፡
የንጉሳዊ አስተዳደሩን የሚቃወሙት፣ ግራ ዘመም ርዕዮት አለም እንከተላለን የሚሉት እነ ሌኒን ከተሰደዱባቸው ሃገሮች ተሳባስበው በእንግሊዝ የቦልሼቪክ ፓርቲን መሰረቱ፡፡
ንጉሳዊ አስተዳደሩን፣ በሰራተኛው መሪነት በሚመሰረት መንግስት ለመተካት፣ ቀስቀሱ፡፡
የመሬት ላራሹን ጥያቄና የፋብሪካ ምርቶችን ተጠቃሚነት አንስተው ገበሬውንና የሰራተኛው ክፍል ለለውጥ አነቃቁት፡፡
የሚመሰረተው ሶሻሊስታዊ መንግስት፣ የሚመራው በሰራተኛው አምባገነንነት ነው አሉ፡፡
ሩሲያ፣ በአንደኛው የአለም ጦርነት ተካፋይ መሆኗን፣ አደገኛና የንጉሳዊ መንግስቱ ግድየለሽነት ነው ብለው ሰበኩ፡፡
“ልጆቻችን ያለቁት ፣ በማያስፈልግ ጦርነት ነው” የሚለው መልዕክታቸው የህዝቡን ስሜት ሳበ፡፡
አንደኛው የአለም ጦርነት፣ በሩሲያ ከፍተኛ ሽንፈትና ውድቀት ማስከተሉ፣ በኑሮ ውድነትና በተዋጊዎቹ እልቂት ሆድ የባሰው ህዝብ፣ ቁጣው እንዲገነፍል አደረገው፡፡
ጦርነቱንም የሚመሩት ራሳቸው ንጉሱ ስለነበሩ፣ ቁጣውና ምሬቱ በዳግማዊ ኒኮላስ ላይ ሆነ፡፡
ወታደሮች በቁጣ ጠመንጃቸውን በአለቆቻቸው ላይ አዞሩ፡፡
ከተሞች በከፍተኛ የህዝብ የአመፅ ማዕበል ተናወጡ፡፡
ሰልፈኞቹ በፒትስበርግ የሚገኘውን ቤተ መንግስት፣ ሰብረው ገቡበት፡
ሁሉም ነገር ከቁጥጥር ውጭ ሲሆን፣ ንጉሱ ስልጣን ለቀው ጊዜያዊ መንግስት ተቋቋመ፡፡
ሌኒን ከነበረበት የስደት ሃገር ፣ወደ ሩሲያ ገብቶ፣ ከፓርቲው አባሎች ጋር አመፅን እንዲቀጣጠል አስተባበረ፡፡
በ1910 ጥቅምት 27 ቦልሼቪክ ፓርቲ፣ ጊዜአዊ መንግስቱን በህዝቡ አመፅ አባሮ ስልጣን ያዘ፡፡
በአለም፣ የመጀመሪያ የሆነውን የሶሻሊስት መንግስት የመሰረተው በሶቪየት ህብረት የመሰረተው የቦልሼቪክ ፓርቲ፣ ስልጣን ሲቆጣጠር ሌኒን የመጀመሪያው ሊቀመንበሩ ሆነ፡፡
ቦልሼቪክ በጀመረው ኮሚዩኒስታዊ ሥርዓት ሶቪየት ህብረት ለ75 አመት ቆየች፡፡
በሩሲያ የኮሚዩኒስት ፓርቲው ቦልሼቪክ ስልጣኑን በሀይል ከወሰደ፣ ዛሬ 107 ዓመት ሞላው፡፡
እሸቴ አሰፋ
SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station in Ethiopia. We are proud to be Ethiopian and we love our country more than anything!
Sheger Radio | Sheger 102.1FM © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.
ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡
ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
#Ethiopia #ShegerFM #ShegerRadio #YekidameChewata #MeazaBirru #Mekoya #EsheteAssefa #TizitaZeaRada #TeferiAlemu #AbebeBalcha #ShegerCafe #ShegerWerewoch #ShegerShelf #ShegerMezenagna #WendimuHailu #ShegerSport #YealemQunqua #EndalkEnaMahider #AderechArada #Woyaddissabeba #GirmaFisseha #ማንን_ምን_እንጠይቅልዎ #መቆያ #የቅዳሜጨዋታ #ሸገርሬድዮ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: t.ly/Sheger
Website: t.ly/ShegerFM
YouTube: t.ly/SHEGER
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Sheger FM 102.1 Radio is The First Private FM Radio Station in Ethiopia
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz Receive SMS online on sms24.me
TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.
Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.
Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.
TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.
Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.
@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.
By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.
Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.
Look for new videos or channels and share them with your friends.
You can start using our bot from this video, subscribe now to በሩሲያ የኮሚዩኒስት ፓርቲው ቦልሼቪክ ስልጣኑን በሀይል ከወሰደ፣ ዛሬ 107 ዓመት ሞላው!
What is YouTube?
YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.