የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በተቋሙ ተልዕኮ ላይ ከፓርላማ ጥያቄ ቀረበበት።
ህዳር 8 2018የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ባለፉት 3 ወራት ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ተከትሎ በተቋሙ ተልዕኮ ላይ ከፓርላማ ጥያቄ ቀረበበት።
በተቋሙ ላይ ጥያቄ የተነሳበት አገልግሎቱ የ3 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርቱን በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ከሰዓት በፊት ባቀረበበት ወቅት ነው።
የተቋሙን የ3 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርት በንባብ ያቀረቡት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ባለፉት 3 ወራት ከ545,000 በላይ የሚሆኑ ዜጎች የፓስፖርት አገልግሎት አግኝተዋል ብለዋል።
ከዚህ ውስጥ ለ373,000 በላይ ዜጎች መደበኛ፣ ከ136 በላይ ለሚሆኑት አስቸኳይ ፣ ከ14,000 በላይ ኢ-ፓስፖርት እንዲሁም ከ20,000 በላይ ለሚሆኑት ደግሞ በቆንጽላ በኩል በአጠቃላይ ከ545,000 በላይ ዜጎች አገልግሎት ተሰጥቷል ሲሉ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
በሩብ ዓመቱ ለመስጠት ታስቦ የነበረው ፖስፖርት መጠን ከ780,000 በላይ እንደነበርም ተጠቅሷል።
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ባለፉት 3 ወራት ከሰጠው አገልግሎት 11 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 10.5 ቢሊዮን ብር እንዳሰበሰበ እና ይህም የእቅዱን 96 በመቶ እንደሆነ ተናግሯል።
የሪፖርቱን ማብቃት ተከትሎ ጥያቄ የጠየቁት አቶ ሳዲቅ አደም የተባሉ የምክር ቤት አባል የተቁሙን የቁጥጥር አቅምን ማደግ አድንቀው በሩብ ዓመት የተሰጠው የፓስፖርት አገልግሎትም የተሻለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አቶ ሳዲቅ “ነገር ግን ተቋሙ ከተሰጠው ሃላፊነት አንጻር ወደ ገቢ መሰብሰብ አላመዘንም ወይ “ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በሩብ ዓመቱ ወደ 11 ቢሊዮን ለመሰብሰብ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ማቀዱን ያስታወሱት የምክር ቤት አባሉ የገልግሎቱ ቀዳሚ ግብ ገቢ መሰብሰብ ነው ወይስ? አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ነው ካሉ በኋላ ማብራርያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡
አገልግሎቱ ገቢ ላይ ትክረቱን አድርጓል በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ የሰጡት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የምንሰጠው አገልግሎት ስለሆነ በዚህም ብዙ ገንዘብ እንደሚሰበሰብ ተናግረዋል፡፡
የተቋሙ ባህሪ አገልግሎት መስጠት ነው በዚህም በተለያ የውጭ አገር ሰዎች ሲመጡ ቪዛ እንሰጣለን ይህ አገልግሎት ደግሞ በየትኛውም አለም በገንዘብ የተተመነ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
በግባችን መሰረት ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ እና ወደ ብሔራዊ ቋት ማስገባት ካልቻልን የተቋሙን አቅም ማሳደግ እንችላለን ማለት አንችልም ብለዋል ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፡፡
የተቋሙ ገቢ ባደገ ቁጥር ለራሱም የሚጠቀመው ከሚሰበስበው ስለሆነ ሁሌ የሚለምን ተቋም መሆን የለበትም ምክንያቱ ደግሞ ቴክኖሎጂው በየጊዜው ስለሚቀያየር ሲሉ እራሱን ማሻሻል እንዳለበት ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ ቀደምም በመንግስት ስም አገልግሎቱ ገቢ እንደሚሰበስብ የተናገሩት ወ/ሮ ሰላማዊት እኛ ያደረግነው የቀድሞውን ወይንም የነበረውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ ነው ብለዋል፡፡
ሰዎች ብዙ ጊዜ ገቢው የሚሰበሰበው ከፓስፖርት ይመስላቸዋል እሱን ግን ስህተት ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ከገቢው ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ግን ከቪዛ እና ተያያዥ አገልግሎቶች መሆናቸውን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ሶስት ወራት ወደ አገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ ከ3,400 በላይ የውጭ አገር ዜጎች መያዛቸውንም የተያዙ አገልግሎቱ ጠቁሟል፡፡
ከዚህ ውስጥ ሊወጡ ሲሉ የተያዙት 1,500 በላይ ሲሆኑ፤ ከ10,900 በላይ ኢትዮጵያውን ደግሞ በህገ-ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጡ ሲሉ ባለፉት 3 ወራት ተይዘዋል ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. https://tinyurl.com/shr5p9zb
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
🐦X : https://x.com/shegerfm?s=2 Receive SMS online on sms24.me
TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.
Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.
Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.
TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.
Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.
@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.
By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.
Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.
Look for new videos or channels and share them with your friends.
You can start using our bot from this video, subscribe now to የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በተቋሙ ተልዕኮ ላይ ከፓርላማ ጥያቄ ቀረበበት።
What is YouTube?
YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.