ባይደን ከዩክሬይን ጋር አዲስ የጸጥታ ስምምነት ተፈራረሙ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እና የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዜለንስኪ ለአስር ዓመታት የሚዘልቅ የጸጥታ ስምምነት ትላንት ሐሙስ ተፈራርመዋል።⁣

ጣሊያን ውስጥ እየተካሄደ ካለው የቡድን ሰባት የመሪዎች ጉባዔ ጎን የተፈረመው ስምምነት የዩክሬይን የመከላከይ ኃይሎች የሩስያን ወረራ የመመከት ዓቅም ለማጠናከር የታለመ መሆኑ ተመልክቷል።⁣

ቀጣይ የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደሮች የቀድምው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በመጪው ምርጫ ቢያሸንፉ እንኳን ጭምር ዩክሬይንን እንዲረዱ ግዴታ የሚያደርግ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ገልጸዋል።⁣

"ዓላማችን የዩክሬይንን የመከላከያ ዓቅም በዘላቂነት ማጠናከር ነው" ያሉት ፕሬዚደንት ባይደን "የዩክሬይን ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ያለበት አሁን ባላት ጥቃትን የመከላከል አቅም እንዲሁም ወደፊትም የሚከሰቱ ወረራዎችን ለመመከት በሚኖራት ብቃት ላይ ሊሆን ይገባል" ብለዋል።⁣

የዩክሬይን ፕሬዚደንት በበኩላቸው "ስምምነቱ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በሚያስፈልጉ እርምጃዎች ላይ ያተኮረ እንደመሆኑ መላውን ዓለም የሚጠቅም ነው። ሩስያ ዩክሬይን ላይ የምታካሂደው ጦርነት በመላው ዓለም ላይ የተደቀነ ተጨባጭ ስጋት ስለሆነ" ብለዋል።⁣

በስምምነቱ ላይ እንደተጠቀሰው ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬይን የጦር መሣሪያዎች፥ የተተኳሾች እና የስለላ መረጃዎች ማጋራት ድጋፍ ታደርጋለች። ስምምነቱ ዩክሬይን ወደፊት የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት አባል እንድትሆን የሚያመቻች እርምጃም እንደሚሆን ተመልክቷል።⁣

ከዚህም ሌላ ጣሊያን ውስጥ ጉባዔ ላይ ያሉት የቡድን 7 መሪዎች ለዩክሬይን የ50 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለመስጠት በመርህ ደረጃ ትላንት ሐሙስ ተስማምተዋል። የብድሩ ዕዳ የሚከፈለው ሩሲያ ዩክሬይን ላይ ወረራ በከፈተችበት ጊዜ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እንዳታንቀሳቅስ ከታገደባት ገንዘብ በሚገኘው ወለድ እንደሚሆን ተጠቁሟል።⁣

በሌላ በኩል የዩክሬይን ጦርነት መቀጠሉን በተመለከተ የነቀፌታ አስተያየት የሚሰጡት የቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በአንድ ወቅት "እኔ አስተዳደሩን በተረከብኩ በመጀመሪያው ቀን አስቆመዋለሁ" ሲሉ ተደምጠዋል።⁣

ትረምፕ ትላንት ሐሙስ በዋሽንግተን ከዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ጋር የተገናኙ ሲሆን በሪፐብሊካን የኮንግሬሱ አባላት ድጋፍ ለዩክሬይን የጸደቀውን የ60 ቢሊዮን ዶላር እርዳት እንደነቀፉ የምክር ቤት አባላቱ ጠቁመዋል።⁣

- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -
🔷 የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሊንኮችን በመጫን ይከተሉን።
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/voaamharic
ኢንስታግራም - https://www.instagram.com/voaamharic
X - https://www.twitter.com/VOAAmharic
ዌብሳይት - https://amharic.voanews.com
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ፡- https://www.youtube.com/voaamharic
የስልክ መሥመራችን 202-205-9942 የውስጥ መሥመር 14 ነው።
📜 ቪኦኤ-አማርኛ ስለ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ አፍሪካ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ዓለም አቀፍ በዲጂታል፣ በራዲዮና በቴሌቪዥን ዜናና ዘገባዎችን ለአድማጭና ለተመልካች ያቀርባል።
VOA Amharic reaches our audience on digital, radio, and TV, delivering news and content about Ethiopia, Eritrea, Africa, and the United States. We will also be bringing you Health Shows, Youth Shows, Democracy Field, Women’s Shows, and Sports Shows on different days, stay tuned. Receive SMS online on sms24.me

TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.

Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.

Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.

TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.

Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.

@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.

By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.

Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.

Look for new videos or channels and share them with your friends.

You can start using our bot from this video, subscribe now to ባይደን ከዩክሬይን ጋር አዲስ የጸጥታ ስምምነት ተፈራረሙ

What is YouTube?

YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.