የተባለውን ያህል ምርት ከተመረተ፤ የምርት ገበያው መረጋጋት ለምን ተሳነው?

ታህሳስ 28/2018

ተመርቷል የሚባለው ምርት ወደ ገበያ በፍጥነት እንዳይደርስ የመንገድ መሰረተ ልማት ምቹ አለመሆን፣ ገበያው በህገወጥ ደላሎች መዘወሩና የህብረት ስራ ማህበራት ደካማ መሆን እንደ ምክንያትነት በባለሞያዎች ተነስቷል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት 1.5 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ኢትዮጵያ ውስጥ መመረቱን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

ነገር ግን ዛሬም የእህል ገበያው በምርት እጥረት ፣ የጥራጥሬና አዝዕርት ገበያው በዋጋ መናር ሲታመስ ይታያል፡፡

መንግስት የህብረተሰቡን ሌማት ሙሉ እንዲሆን ለማድረግ ምርትን ለማትረፍረፍ፣ ገበያውን ለማረጋጋት የተለያየ ስራ ቢሰራም መሬት ላይ የታሰበውን ያህል ለውጥ ሲያመጣ አይታይም፡፡

የምርት ዋጋ መናር ለምን በየጊዜው ይታያል? የተባለውን ያህል ምርት ከተመረተ የምርት ገበያው መረጋጋት ለምን ተሳነው፤ አግሮ ኢኮኖሚስት የሆኑትን ታደለ ማሞን(ዶ/ር) ጠይቀናቸዋል፡፡

ታደለ ማሞ(ዶ/ር) በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የግብርና ኢኮኖሚ ምርምር ዳይሬክተር እና ተመራማሪ ናቸው፡፡

እርሳቸው እንደሚሉት ገበያው እንዳይረጋጋ፣ ተመርቷል የተባለው ምርት ሸማቹ ጋር በአግባቡ እንዳይደርስ ህገ-ወጥ ነጋዴዎችና ደላሎችን ተጠያቂ ናቸው፡፡

በዚህም ምክንያት ገበያው በደላሎች እጅ እንዲወድቅና በነሱ ብቻ እንዲዘወር አድርጓል፡፡

ከዚህ ባለፈም ገበሬው ዛሬም ድረስ የሚያመርትበት መንገድ ባህላዊ መንገድ ስለሆነ ከፍተኛ ወጪ እንዲያወጣ ያደርገዋል ይህም የምርት ዋጋው እንዲንር ያደርገዋል ሲሉም ያስረዳሉ፡፡

ከእርሻ እስከ አጨዳ ድረስ በሰው ሀይል ነው የሚከወነው ይህ እስካሁን አልተቀየረም ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ገበሬው እያገኘ አይደለም በማለት ጠቅሰዋል፡፡

ቀደም ባለው ጊዜ መንግስት የህብረት ስራ ማህበራት እና ሸማች ማህበራት አደራጅቶ አስገብቶ ነበር እነዚህ ማህበራት በትክክለኛ ባለሞያ ባለመመራታቸው የታሰበው ለውጥ ማምጣት አልቻሉም ብለዋል ዶክተር ታደለ ማሞ፡፡

መንግስት በየጊዜው ተመርቷል ሲል ሚናገረው ምርት በቀጥታ ሸማቹ ጋር እንዲደርስ ከፈለገ አምራችና ሸማቾች መካከል ያሉ ህገወጥ ነጋዴዎችንና ደላሎችን መቆጣጠር አለበት ይላሉ፡፡

የተቋቋሙ ሸማች ማህበራትን አቅም ማሳደግና በትክክለኛ ባለሙያ እንዲመሩ በማድረግ ገበያው ውስጥ በስፋት እንዲገቡ ቢደረግ የዋጋ ንረቱንና የምርት አቅርቦት እጥረቱን ማስተካከል ይቻላል ይላሉ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የግብርና ኢኮኖሚስት ምርምር ዳይሬክተር እና ተመራማሪው ዶክተር ታደለ ማሞ፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….

በረከት አካሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://youtube.com/@shegerfm1021radio?si=MIGhci0wINMYwCmw
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1
WhatsApp : https://whatsapp.com/channel/0029VaAOnG9J3juypE0M4G1O
X : https://x.com/shegerfm?s=2 Receive SMS online on sms24.me

TubeReader video aggregator is a website that collects and organizes online videos from the YouTube source. Video aggregation is done for different purposes, and TubeReader take different approaches to achieve their purpose.

Our try to collect videos of high quality or interest for visitors to view; the collection may be made by editors or may be based on community votes.

Another method is to base the collection on those videos most viewed, either at the aggregator site or at various popular video hosting sites.

TubeReader site exists to allow users to collect their own sets of videos, for personal use as well as for browsing and viewing by others; TubeReader can develop online communities around video sharing.

Our site allow users to create a personalized video playlist, for personal use as well as for browsing and viewing by others.

@YouTubeReaderBot allows you to subscribe to Youtube channels.

By using @YouTubeReaderBot Bot you agree with YouTube Terms of Service.

Use the @YouTubeReaderBot telegram bot to be the first to be notified when new videos are released on your favorite channels.

Look for new videos or channels and share them with your friends.

You can start using our bot from this video, subscribe now to የተባለውን ያህል ምርት ከተመረተ፤ የምርት ገበያው መረጋጋት ለምን ተሳነው?

What is YouTube?

YouTube is a free video sharing website that makes it easy to watch online videos. You can even create and upload your own videos to share with others. Originally created in 2005, YouTube is now one of the most popular sites on the Web, with visitors watching around 6 billion hours of video every month.